በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የወግ አጥባቂው ፓርቲ አባል ሪሺ ሱናክ አዲሱ የእንግሊዝ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነዋል   


ንጉሥ ቻርለስ ሶስተኛ ሪሺ ሱናክን በበኪንግሃም ቤተመንግስት ተቀብለው ሹመታቸውን ሲያፀድቁ
ንጉሥ ቻርለስ ሶስተኛ ሪሺ ሱናክን በበኪንግሃም ቤተመንግስት ተቀብለው ሹመታቸውን ሲያፀድቁ

ሪሺ ሱናክ ዛሬ ማክሰኞ የጠቅላይ ሚኒስትርነቱን ሥልጣን የተረከቡት ሊዝ ትረስ ሥልጣናቸውን በገዛ ፈቃዳቸው ከለቀቁ በኋላ ነው፡፡

ሊዝ ትረስ መልቀቂያቸውን በይፋ ለንጉሥ ቻርለስ ለማቅረብ ወደበኪንግሃም ቤተ መንግሥት ከማምራታቸው በፊት ዛሬ በ10 ዳዊኒንግ ስትሪት ደጃፍ ላይ አጭር የስንብት ንግግር አድርገዋል፡፡

ሊዝ ትረስ መልቀቂያቸው አቅርበው ከቤተ መንግሥቱ ሲወጡ ንጉሥ ቻርልስ ተተኪያቸውን ሪሺ ሱናክን ተቀብለው ካነጋገሯቸው በኋላ መንግሥታቸውን እንዲመሰርቱ በይፋ ጋብዘዋቸዋል፡፡

በምጣኔ ሀብት ቀውስ ውስጥ የምትገኘው ብሪታኒያን እንደሚመሩ ቃል የገቡት ሱናክ በእንግሊዝ የ200 ዓመት ታሪክ በእድሜ ትንሹና የመጀመሪያው ነጭ ያልሆኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ናቸው፡፡

ሱናክ አዲሱ መኖሪያቸው ከሚሆነው ከ10 የዳውኒንግ ስትሪት ደጃፍ ባሰሙት ንግግር ተሰናባቿን ጠቅላይ ሚኒስትር አመስግነዋቸዋል፡፡

የትረስ የኢኮኖሚ እድገት እቅድ ስህተት አልነበረም፣” ያሉት ሱናክ ይሁን እንጂ “ስህተቶች ተሰርተዋል” ብለዋል፡፡

አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር “በፓርቲዬ መሪነትና ጠቅላይ ሚኒስትራችሁ ሆኜ የተመረጥኩት አንድም እነዚህን ችግሮች እንዳስተካክል ነው” ብለዋል፡፡

ሪሺ ሱናክ አሁን አዲሱን ካቢኒያቸውን የሚያቋቋሙሲሆን ፣ የወግ አጥባቂው ፓርቲ ህግ አውጭዎች፣ ካቢኔው ውስጥ ከፓርቲው የሚመረጡ ፖለቲከኞች ይካተቱበታል ብለው ተስፋ ማድረጋቸው ተመልክቷል፡፡

XS
SM
MD
LG