በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአውሮፓ ህብረት ለዩክሬን ፈጣን መልሶ ግንባታ ድጋፍ እንዲሰጥ አሳሰበ  


 የአውሮፓ ኮሚሽን ፕሬዚዳንት ኡርሱላ ቮን ደር ላየን (ፎቶ ፋይል)
የአውሮፓ ኮሚሽን ፕሬዚዳንት ኡርሱላ ቮን ደር ላየን (ፎቶ ፋይል)

በሩሲያ ኃይሎች ሲቪላዊ መሰረተ ልማቷ የመውደም አደጋ የተረጋጠባት ላልዋት ዩክሬን “ፈጣን መልሶ ማቋቋም” ሊደረግላት እንደሚገባ የአውሮፓ ኮሚሽን ፕሬዚዳንት ኡርሱላ ቮን ደር ሌየን አሳሰቡ፡፡

ቮን ደር ሌየን በዩክሬን መልሶ ማቋቋምና ግንባታ ላይ ለመወያየት በበርሊን በተዘጋጀው ጉባኤ ላይ ባደረጉት ንግግር “ሩሲያ ክረምቱ እየተቃረበ ሲመጣ ዩክሬንን ከውሃ፣ ከሙቀትና ከመብራት ኃይል አገልግሎት ለማቆራረጥ በግልጽ እየሰራች ነው” ብለዋል፡፡ እንዲህ ያሉ የሩሲያ ጥቃቶች “ግልጽ የሽብር ተግባር ናቸው” ሲሉም አክለዋል፡፡

ቮን ዴር ለየን ሩሲያ ወረራዋን ከሰነዘረች 8 ወራት በኋላ ያለውን ውድመት “እጅግ አስደንጋጭ” ሲሉ ገልጸውታል፡፡

የአውሮፓ ኮምሽን ፕሬዚዳንቷ አያይዘውም “ይህ ለዩክሬናውያን እጅግ ከባድ፣ አስፈሪ እና የስቃይ ጊዜነው፣ ዩክሬናውያን ግን ተስፋና በራስ መተማመን ያላቸው መሆኑንና ለዚህም መፋለማቸውን የሚቀጥሉ መሆኑን እያሳዩን ነው፤ ዛሬ እኛ እዚህ የሰበሰብንም ይህ የወደፊት ተስፋቸው ነው” ብለዋል፡፡

በጉባኤው ላይ የመንግሥታት፣ የትምህርት እና የምርምር ተቋማት እንዲሁም ከዓለም አቀፍ ድርጅቶች የተውጣጡ ተሳታፊዎች የተካተቱበት እንደሆነም ተመልክቷል፡፡

ውይይቱ ለዩክሬን በሚያስፈልጉ የቅድሚያ ጉዳዮችና ያሉትን የፋይናንስ ፕሮጀክት አማራጮችን የሚያካትት መሆኑን የአውሮፓ ህብረት አመልክቷል፡፡

በስብሰባው ላይ ቃል የሚገባ ምንም ዓይነት የፋይናንስ ድጋፍም ሆነ የፖለቲካ ስምምነቶች እንደማይጠበቁ ተገልጿል፡፡

የዩክሬን መንግሥት፣ የአውሮፓ ህብረት ኮሚሽንና የዓለም ባንክ ባላፈው መስከረም ባወጡት ዘገባ ከሩሲያ ወረራ በኋላ ዩክሬንን መልሶ ለመገንባት 350 ቢሊዮን ዶላር ሊያስወጣ እንደሚችል አስታውቀዋል፡፡

የዓለም ባንክ ትናንት ሰኞ በብሪታኒያና በተደገፈ የብድር ዋስትና ለዩክሬን መንግሥት መሰረታዊ አገልግሎቶች የሚውል የ500 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ መስጠቱ ተገልጿል፡፡

XS
SM
MD
LG