በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ታይዋን ዓለም አቀፍ የዴሞክራሲ ተሟጋቾችን ስብሰባ አስተናገደች   


የታይዋን ፕሬዝደንት ሳይ ኢንግ-ወን (ፎቶ ፋይል)
የታይዋን ፕሬዝደንት ሳይ ኢንግ-ወን (ፎቶ ፋይል)

በአምባገነን አገዛዞች የተደቀነው ስጋት “በመላው ዓለም ላሉ ዴሞክራቶች የማንቂያ ደወል ነው” ሲሉ የታይዋን መሪ ፕሬዚዳንት ታይ ኢንግ ወን ዛሬ ተናገሩ፡፡

ፕሬዚዳንቷ ይህን የተናገሩት የሆንግ ኮንግን ብሄራዊ የናታን ህግን በመቃወም የተሰደዱትን ጨምሮ ዓለም አቀፍ የዴሞክራሲ ተሟጓቾች የተገኙበትን ስብሰባ ሲከፍቱ ባሰሙት ንግግር ነው፡፡

ታይፔይ ውስጥ በተከፈተው ስብሰባ ኢራን ሩሲያ እና ዩክሬንን ጨምሮ ከ70 አገሮች የተውጣጡ 200 የሚደርሱ የፖለቲካ እና የሲቪክ መሪዎች መካፈላቸው ተመልክቷል፡፡

ስብሰባው የተጀመረው የቻይናው ፕሬዚዳንት ሺ ጂፒንግ ሥልጣናቸውን ለሶስተኛ ጊዜ ያጠናከሩበትንና ታማኞቻቸውን ወደ ከፍተኛ የስልጣን እርከን ያሸጋገሩበትን የተቀነባበረ የኮሙዩኒስት ፓርቲ ስብሰባ ተከትሎ ነው፡፡

ዲሞክራሲያዊት ታይዋን ደሴቲቱን የግዛቷ አካል አድርጋ በምትመለከታት ቻይና አንድ ቀን ልትወሰድ እንደምትችል ተከታታይ በሆነ የወራር ስጋት ስር ትገኛለች ሲል የአዣንስ ፍራንስ ፕሬስ ዘገባ አመልክቷል፡፡

XS
SM
MD
LG