በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በዩክሬን የኃይል ማመንጫዎች ላይ ያነጣጠረ "መጠነ-ሰፊ" ጥቃት ሩሲያ መፈጸሟ ተነገረ።


ምስሉ ጥቅምት 18/2022 በሩሲያ ጥቃት የደረሰበትን የኃይል ማመንጫ ጣቢያ ለማትረፍ የሚጥሩ የእሳት አደጋ ሰራተኞችን ያሳያል ።
ምስሉ ጥቅምት 18/2022 በሩሲያ ጥቃት የደረሰበትን የኃይል ማመንጫ ጣቢያ ለማትረፍ የሚጥሩ የእሳት አደጋ ሰራተኞችን ያሳያል ።

ሩሲያ በሰላማዊ ሰዎች መጠቀሚያ የኃይል አውታሮች ላይ “መጠነ-ሰፊ” ጥቃት በመከፍቷ ምክንያት ሀገር አቀፍ የኃይል መቋረጥ እንደ ተከሰተ ፣ የዩክሬኑ ፕሬዚደንት ቭሎድሜር ዘለንስኪ ትናንት በቪዲዮ በተላለፈ ንግግራቸው አስታወቁ።

የዩክሬን ባለስልጣናት በሀገሪቱ የሚገኙ 1.5 ሚሊየን ቤቶች ያለ ኤልክትሪክ ኃይል እንደቀሩ አስታውቋል ። ዘለንስኪ ግን አብዛኞቹ የሩሲያ ሚሳዬሎች እና ድሮኖችን ተመተው መጣላቸውን በመግለጽ ቀደም ብሎ በሀገራቸው የጦር ኃይል በኩል ፣ ከምድር እና ከባህር ከተነሱ 33 ሚሳኤሎች መካከል 18ቱን ማክሸፋቸው ተጠቅሶ የተገለጸውን መግለጫ በድጋሚ አጠናክረዋል።

ሀገራቸው ሙሉ በሙሉ የሩሲያን ጥቃት ለመመከት የሚያበቃ አቅም በአሁኑ ጊዜ ባይኖራትም ፣ ከአጋሮቻቸው ጋር በመሆን በአስፈላጊው ደረጃ ላይ ቀስ በቀስ እንደሚደደርሱ ርግጠኛ መሆናቸውን ዘለንስኪ አስታውቀዋል።

በአለፉት ሁለት ሳምንታት ሩሲያ በዩክሬን የኃይል ጣቢያዎች ፣ የውሃ አቅርቦት ስርዓት እና ሌሎች ቁልፍ መሰረተ ልማቶች ላይ ጥቃቷን አጠናክራለች ። ዘለንስኪ በጥቃቶቹ ምክንያት የኃይል መቆራረጥ የገጠማቸው ግዛቶችን ኃይል መልሶ ለማንሰራራት መቻሉንም ጠቁመዋል ።

ከአውሮፓዊያኑ ጥቅም 10 ወዲህ በተከፈቱ ጥቃቶች ብቻ የዩክሬን 30 በመቶ የኃይል ጣቢያዎች መውደማቸውን ዘለንስኪ ተናግረዋል።የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ደኒስ ሺምያል በበኩላቸው የበረታው የሚሳኤል እና የድሮን ጥቃት አዲስ የዩክሬናዊያን ስደተኞችን ማዕበል እንዳያስከትል አስጠንቀዋል። “በዩክሬን፣ የኤልክትሪክ ኃይል፣ የማመቆቂያ አቅርቦት፣ ውሃ ከሌለ ይሄ አዲስ የስደተኞች ሱናሚ ይፈጥራል” ብለዋል ፍራንክፈርተር አልገማይን ዥተንግ ለተሰኘ የጀርመን የዜና አውታር።

XS
SM
MD
LG