በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ጉዳይ የዛሬ (ረቡዕ) መረጃ


የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ጉዳይ የዛሬ (ረቡዕ) መረጃ
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:09 0:00

የሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት ተባብሶ በቀጠለበት በዚህ ወቅት ግጭቱ በትግራይ ክልል የሚያካሂደውን የሰብዓዊ ዕርዳታ አቅርቦት እንቅስቃሴ እያስተጓጎለበት እንደሆነ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ገለፀ፡፡

የተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ጽ/ቤት (ዩኤንኦቻ)፣ “ግጭቱ ሰብዓዊ ድርጅቶች ወደሚንቀሳቀሱባቸው አካባቢዎች በመቅረቡ የዕርዳታ እንቅስቃሴያቸውን ውስን እያደረጉ ነው” ብሏል። በሌላ በኩል ዓለምአቀፉ የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋች ድርጅት ሂዩማን ራይትስ ዋች በሽረ እና አካባቢው ግድያና ሌሎች የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ሊፈጸሙ ይችላሉ የሚል ሥጋት መጨመሩን አመልክቷል።

የኢትዮጵያ መንግሥት በበኩሉ አካባቢዎቹን ያለምንም የከተማ ውስጥ ጦርነት ተቆጣጥረናል” ሲል አስታውቋል፡፡

የኢትዮጵያ መንግሥት ማምሻውን ባወጣው መግለጫም የፌደራሉ የመከላከያ ሠራዊት በተቆጣጠራቸው አካባቢዎች የዕርዳታ አቅርቦትን ለማሳለጥ ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት፣ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ ከብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት፤ ከሀገር መከላከያ ሠራዊት፣ ከፌደራል ፖሊስ እንደዚሁም ከኢትዮጵያ የአደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን የተውጣጣ ኮሚቴ ተዋቅሮ ወደ ሥራ መግባቱን አስታውቋል።

[ሙሉውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ያገኛሉ]

XS
SM
MD
LG