የሞቃዲሹ መንግስት የሃገሪቱ ነጋዴዎች ለአል-ሸባብ የሚፈጽሙትን ክፍያ እንዲያቆሙ አስጠንቅቋል። ይህም አል-ሻባብ የሽብር ተግባሩን ለማከናወን በማስፈራራት የሚሰብስበውን ዳጎስ ያለ ክፍያ ለማስቆም ነው ተብሏል።
የሶማሊያ የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር በመግለጫው እንዳለው የአል-ቃይዳ ሸሪክ ለሆነው አል-ሻባብ ክፍያ የሚፈጽሙ ጋዴዎች ሕጉ ሙሉ ለሙሉ ተፈጻሚ ይሆንባቸዋል ። የንግድ ፈቃዳቸው ተነጥቆ፣ ንብረታቸው እንደሚወረስ ሚኒስቴሩ አስጠንቅቋል ሲል ኤ.ኤፍ.ፒ ዘግቧል።
አል-ሻባብ በውስብስና ሰፊ በሆነ የግብር ሥርዓት በሚሊዮን ዶላር የሚቆጠር ገንዘብ እንደሚሰበስብ ጉዳዩን የሚያጠኑ ባለሙያዎች ይናገራሉ።
አል-ሻባብ ላለፉት 15 ዓመታት መንግስትን ለማስወገድ ሲዋጋ ቆይቷል። ስፊ ግዛትን የሚቆጣጠር ሲሆን፣ በማስፈራራት ታክስ ይሰበስባል።
ቡድኑ የንብረት እንዲሁም በኬላዎች ላይ የጭነት ግብር፣ በተጨማሪም በመዲናዋ ወደብ የሚያልፉና ወደ ሃገር በሚገቡ ሸቀጦች ላይ ግብር እንደሚጥል በሞቃዲሹ መሠረቱን ያደረገው ሂራል ተቋም ከሁለት ዓመታት በፊት ባወጣው ሪፖርት አስታውቋል።
ተቋሙ እንደሚለው አል-ሸባብ በወር ቢያንስ 15 ሚሊዮን ዶላር የሰበስባል።
አል-ሸባብ ባለፉት ቅርብ ወራት ባደረሰው ጥቃት በበለደወይን 30 ሰዎችን ሲገድል፣ ባለፈው ነሐሴ በሞቃዲሹ አንድ ሁቴል ላይ ባደረገው ጥቃት ደግሞ 21 ሰዎችን ገድሏል።