በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የጀርመኑ መራሄ መንግስት የአውሮፓ ህብረት ሊሻሻል እና ወታደራዊ ራስገዝነት ሊኖር  ይገባል ሲሉ ጥሪ አደረጉ


የጀርመኑ መራሄ መንግስት ኦላፍ ሹልዝ
የጀርመኑ መራሄ መንግስት ኦላፍ ሹልዝ

የጀርመኑ መራሄ መንግስት የአውሮፓ ህብረት ሊሻሻል እና ወታደራዊ ራስገዝነት ሊኖር ይገባል ሲሉ ጥሪ አደረጉ።

የጀርመኑ መራሄ መንግስት ኦላፍ ሹልዝ የአውሮፓ ሕብረት አዲስ አገሮችን እንዲቀበል እና በስሩ ላሉ 27 አገሮች ወታደራዊ ራስ ገዝነትን እንዲፈቅድ ለማስቻል ማሻሻያዎችን ማድረግ አለበት ሲሉ በዛሬው ዕለት ጥሪ አቅርበዋል።

የግብር ፖሊሲን እና ሌሎች ጉዳዮችን ጨምሮ በውጭ ፖሊሲዎች ውስጥ ለሚደረጉ ውሳኔዎች የአንድነት መርሆዎች ቀስ በቀስ እንዲሰረዙ፤ ሲሉም በበርሊን የአውሮፓ ሶሻሊስቶች ፓርቲ ኮንግረስ ላይ ንግግር ባደረጉበት ሰዓት ቀስቅሰዋል።

“ይህንን ለማድረግ ብዙ የማሳመን ስራዎችን መስራት እንዳለብን አውቃለሁ” ያሉት ኦላፍ “ነገር ግን የእኛ ምኞት ጂኦ ፖለቲካዊ አውሮፓን መመስረት ከሆነ የብዙሃን ድምጽ ውሳኔዎች ትርፍ እንጂ ሉዓላዊነትን ማጣት አይደሉም” ብለዋል።

አሁን ባለው አሰራር መሰረት በአውሮፓ የሚወሰኑ ውሳኔዎች በሙሉ ተግባራዊ የሚሆኑት ሁሉም አባል አገሮች ሲስማሙባቸው ብቻ ነው። ሹልዝ ወታደራዊ ራስ ገዝነት እንዲኖር የሚሹ ሲሆን እ.ኤ.አ በመጪው 2025 ዓም በአውሮፓ ህብረት ዋና ጽ/ቤት በአስቸኳይ የሚቋቋም የአውሮፓ ህብረት አባል አገሮች ሰራዊት ይኖር ዘንድ የጋራ የጦር መሳሪያ ግዢ እንዲደረግም ጥሪ አድረገዋል።

“በአውሮፓ ውስጥ በመከላከያ ጥረቶች መካከል የተሻለ መስተጋብር ያስፈልገናል” ነበር ያሉት። በድፍረትን እና በጥምረት አውሮፓ ሃይል ማደርጀት እና ለወደፊቱም የተቀናጀ ኃይል እንዲኖረን አቅማችንን ማዳበር ይኖርብናል፡፡” ብለዋል።

XS
SM
MD
LG