በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በየመን ጊዜው ያለፈበት መድሃኒት የወሰዱ 10 የደም ካንሰር ታማሚ ህጻናት ሕይወታቸው አለፈ


በየመን ሰንዓ በጽኑ ህክምና ላይ የምትገኝ ታካሚ
በየመን ሰንዓ በጽኑ ህክምና ላይ የምትገኝ ታካሚ

በአማጺያኑ ቁጥጥር ስር በሚገኝ በአንድ ሆስፒታል ውስጥ የሚገኙ ሉኪሚያ የተሰኘ የደም ካንሰር በሽታ ተጠቂ የሆኑ አስር የሚሆኑ ጽኑ ታማሚ ህጻናት በተሰጣቸው ጊዜ ያለፈበት መድሃኒት የተነሳ ህይወታቸው ማለፉ ታውቋል። ሌሎች ቁጥራቸው ከአስር በላይ የሚሆኑ ሕጻናት ደግሞ በአስጊ የጤና ሁኔታ ውስጥ እንደሚገኙ የህክምና ባለሞያዎች እና የሆስፒታሉ ሰራተኞች ትላንት አርብ ይፋ አድርገዋል።

በየመን እየተካሄደ ያለውና ከተጀመረ ስምንት ዓመታትን ያስቆጠረው አውዳሚ ግጭት በዓለም እጅግ አስከፊ የሆነ ቀውስ ያስከተለ እና እስካሁን ባለው ከ150 ሺ በላይ ሰዎችን ህይወትን የቀጠፈ ነው።

በአማጺያኑ የሚተዳደረው የጤና ሚኒስቴር በሰንዓ ኩዌት ሆስፒታል ህይወታቸው ያለፉት ልጆች እድሜያቸው ከ3 እስከ 15 እንደሚሆን አስታውቋል። አያይዞም ጊዜያቸው ያለፈባቸው መድሃኒቶች በህገወጥ መንገድ በተለያዩ የግል ክሊኒኮች ውስጥ የገቡ ናቸው ብሏል። ይሁን እንጂ ባለስልጣናቱ አስሩ ህጻናት የሞቱበትን ትክክለኛ ጊዜ አላስታወቁም።

አሶሽየትድ ፕሬስ አነጋገርኳቸው ያላቸው ስድስት የሚደርሱ የጤና ኃላፊዎች በህንድ ሃገር የተመረተውን ሜተትሬክሴይት የተሰኘውን እና በህገወጥ መንገድ ወደ ሃገር የገባው ጊዜው ያለፈበትን የካንሰርመድሃኒት ቁጥራቸው 50 ለሚደርስ ሕጻናት እንደተሰጠ ተናግረዋል። ማንነታቸው እንዲታወቅ የማይሹት እነኚህ የጤና ሃላፊዎች እስካሁን ድረስ ሕይወታቸው ያለፉት ህጻናት ቁጥርም 19 መድረሱን ጨምረው ገልጠዋል።

XS
SM
MD
LG