በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በኢትዮጵያው ግጭት የስድስቱ አገሮች መግለጫ እና የወገኖቹ ምላሽ


በኢትዮጵያው ግጭት የስድስቱ አገሮች መግለጫ እና የወገኖቹ ምላሽ
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:01 0:00

“ዩናይትድ ስቴትስን ጨምሮ ስድስት አገሮች ያወጡት መግለጫ የኢትዮጵያን አቋም ያላገናዘበ ነው” ሲል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገለጸ።

ህወሓት ቃል አቀባይ አቶ ጌታቸው ረዳ በበኩላቸው የአገሮቹን የጋራ መግለጫ አድንቀዋል፡፡

ስድስቱ አገሮች በትናንቱ መግለጫቸው የኢትዮጵያ መንግሥት እና ህወሓት ወታደራዊ ግጭቱን በአስቸኳይ እንዲያቆሙና የግጭት ማቆም ሥምምነት እንዲያደርጉ ሲሉ ጠይቀዋል።

በተያያዘ ዜና፣ የአውሮፓ ፓርላማ በቅርቡ ኢትዮጵያን በሚመለከት ያፀደቀውን የውሳኔ ሀሳብ “የኢትዮጵያ ተጨባጭ ሁኔታ ያላገናዘበ” ሲሉ አምባሳደር መለስ ዓለም አጣጥለዋል፡፡

የውሳኔ ሀሳቡን በሚመለከት ከህወሓት ወገን ግን እስካሁን በይፋ የተሰጠ ምላሽ የለም፡፡

[ሙሉውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ያገኛሉ]

XS
SM
MD
LG