በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የፈተና ስርቆትን የመከላከል ጥረቶችና የታዩ ፈተናዎች


የፈተና ስርቆትን የመከላከል ጥረቶችና የታዩ ፈተናዎች
please wait

No media source currently available

0:00 0:08:30 0:00

የዘንድሮው የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በዩኒቨርሲቲዎች እንዲሰጥ ያደረገችው ኢትዮጵያ ኩረጃን እና የፈተና- ስርቆትን የመከላከል ጥረቷን አጠናክራለች።

ሆኖም በአንዳንድ ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ መስተጓጎል ተፈጥሯል።

"በተወሰኑ ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎች አንፈተንም በሚል በመውጣታቸው 12ሺህ 787 ተማሪዎች አልተፈተኑም" ብሏል የትምህርት ሚኒስቴር።

በተለይ በደብረታቦር ዩኒቨርሲቲ በዚሁ ምክንያት በተፈጠረ ግጭት የአንድ ተማሪ ሕይወት ማለፉንና በሌሎች ላይም ጉዳት መድረሱን በመንግሥት የመገናኛ ብዙሃን የተጠቀሰው ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ አስታውቋል።

የሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ ወ/ሮ አመለወርቅ ሕዝቄል ለአሜሪካ ድምፅ በሰጡት ቃል "የትምህርት ሚኒስቴር ኮርጁ ወይም ፈተና ሰርታችሁ ስጡ የሚል ፈቃድ ሊሰጥ አይችልም" ብለዋል።

[ሙሉውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ያገኛሉ]

XS
SM
MD
LG