በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በናይጄሪያ አንድ ጀልባ ሰምጣ 10 ሰዎች ሞቱ


በጎርፍ ምክንያት መንቀሳቀስ ያልቻሉ ናይጄሪያውያን (AP Photo/Fatai Campbell Oct. 7, 2022)
በጎርፍ ምክንያት መንቀሳቀስ ያልቻሉ ናይጄሪያውያን (AP Photo/Fatai Campbell Oct. 7, 2022)

በደቡብ ምሥራቅ ናይጄሪያ ትናንት አንድ ጀልባ ሰምጣ 10 ሰዎች ሞተው 60 ደግሞ የደረሱበት እንዳልታወቀ የአደጋ ምላሽ ባለሥልጣናት ተናግረዋል።

በሃገር ውስጥ የተሠራችው ጀልባ ወደ ገበያ የሚሄዱ 85 ሰዎች ጭና የነበረ ሲሆን ባጋጠማት የሞተር እክል ምክንያት ልትሰምጥ መቻሉ ታውቋል።

የቪኦኤው ቲመቲ ኦቢዪዙ ከአቡጃ እንደዘገበው፣ እስከ አሁን 15 ሠዎች ማዳናቸውን የዕርዳታ ሰራተኞች አስታውቀዋል።

ጀልባዋ ሞተሯ ሲበላሽ፣ ከሰመጠ ድልድይ ጋር ተጋጭታለች ሲሉ ባለስልጣናት ተናግረዋል። አብዛኞቹ ተጓዦች ሴቶች እንደነበሩና ወደ ገበያ ለሥራ እያቀኑ ነበር ተብሏል።

ሰሞኑን በአካባቢው ከፍተኛ ጎርፍ በመከሰቱ፣ ነዋሪዎች ጀልባ ለመጠቀም መገደዳቸውም ታውቋል።

ከያዝነው የፈረንጆች ዓመት ጀምሮ ወደ 300 ያሚጠጉ ሰዎች በጎርፍ አደጋ ሞተዋል ተብሏል።

XS
SM
MD
LG