በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሩሲያ መኖሪያ ቤቶችን በሚሳዬል ደበደበች


ሩሲያን ከክሪሚያ ጋር የሚያገናኘው ድልድይ (Saturday, Oct. 8, 2022. Maxar Technologies via AP)
ሩሲያን ከክሪሚያ ጋር የሚያገናኘው ድልድይ (Saturday, Oct. 8, 2022. Maxar Technologies via AP)

በደቡብ ምሥራቅ በምትገኘው የዩክሬን ከተማ ዛፖሪዥዢያ ላይ ዛሬ ማምሻውን ሩሲያ ባደረገቸው የሚሳዬል ድብደባ፣ ቢያንስ 13 ሠዎች ሲገደሉ፣ ከ 60 በላይ የሚሆኑት ደግሞ ቆስለዋል ሲሉ የዩክሬን ባለሥልጣናት አስታውቀዋል።

ጥቃቱ ሩሲያ አካባቢውን ከግዛቴ ቀላቅያለሁ ማለቷን ለማስረገጥ የተፈጸመ እንደሆነና፣ ነገር ግን ዛፖሪዥዢያ አሁንም በዩክሬን ቁጥጥር ሥር እንደምትገኝ ታውቋል።

በአፓርትመንት ሕንጻዎችና ቤቶች ላይ የተፈጸመው ጥቃት፣ ሩሲያን ከክሪሚያ ጋር የሚያገናኝ ድልድይ በከፊል በቦንብ መፍረሱን ተከትሎ የመጣ ነው ተብሏል።

በእ.አ.አ 2014 ዓ/ም በሩሲያ የተጠቀለለችውን ክሪሚያ የሚያገናኘው ድልድይ፣ ሩሲያ በደቡባዊ ዩክሬን ለምታካሂደው ጥቃት ለሠራዊትና መሳሪያ አቅርቦት ከፍተኛ ጠቀሜታ እንደነበረው ታውቋል።

የዩክሬን ባለሥልጣናት በአጠቃላይ ጥቃት መሰፈጸማቸን አመላክተው፣ ለድልድዩ ጥቃት ግን ቀጥተኛ ኃላፊነት ከመውሰድ ተቆጥበዋል።

“ዛሬ መጥፎ ቀን አልነበረም። ግዛታችን በአብዛኛው ጸሃያማ ነበር። በክሪሚያ ግን ደመናማ ነበር፤ ግን ደግሞ ሙቀትም ነበር” ሲሉ የዩክሬኑ ፕሬዘደንት ቮሎዲሚር ዜሌንስኪ በአግቦ ተናግረዋል።

XS
SM
MD
LG