በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ፍልስጤማዊ ታጣቂ የእስራኤል ወታደርን ተኩሶ ገደለ


የፍልስጤም ወጣቶች ከእስራኤል ወታደች ጋር ሲፋለሙ (September 30, 2022. Photo by JAAFAR ASHTIYEH / AFP)
የፍልስጤም ወጣቶች ከእስራኤል ወታደች ጋር ሲፋለሙ (September 30, 2022. Photo by JAAFAR ASHTIYEH / AFP)

አንድ ፍልስጤማዊ ታጣቂ በእየሩሳሌም ወታደራዊ ኬላ ላይ የነበረች አንዲት የእስራኤል ወታደርን ቅዳሜ ምሽት ተኩሶ መቷል። የ 18 ዓመቷ የእስራኤል ወታደር ሆስፒታል ከደረሰች በኋላ ህይወቷ እንዳለፈ የሀገሪቱ ሠራዊት አስታውቋል።

ሹዋፋት በተባለ የስደተኞች ካምፕ፣ ፍልስጤማዊው ከመኪና ወርዶ በወታደሯና በአንድ የጥበቃ ሠራተኛ ላይ ተኩስ እንደከፈተ ታውቋል።

ሁለት የእስራኤል የድንበር ፖሊሶች በፍንጣሪ ቀላል ጉዳት እንደደረሰባቸው ሰራዊቱ ጨምሮ አስታውቋል።

ድርጊቱ በእስራኤል በተያዘችው ዌስት ባንክ ሁለት ፍልስጤማዊ ታዳጊ ወጣቶች በእስራኤል ሰራዊት የምሽት ጥቃት ወቅት መገደላቸውን ተከትሎ የመጣ ነው ተብሏል።

መሃሙድ አል ሱስ የተባለ የ18 ዓመት ወጣትና አህመድ ዳራግሜ የተባለ የ 16 ዓመት ታዳጊ እንደነበሩም ታውቋል።

የእስሬላውያንና የፍልስጤማውያኑ ሁከት ሰሞኑን እያየለ መጥቷል። ተከታታይ ሞትን ያስከተሉ ጥቃቶች እስራኤል ውስጥ ከተፈጸሙ በኋላ፣ የእስራኤል ሰራዊት በዌስት ባንክ ውስጥ የምሽት ወታደራዊ ጥቃት በማድረስ ላይ ነው ሲል አሶስዬትድ ፕረስ ዘግቧል።

XS
SM
MD
LG