በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሰሜን ኮሪያ በሌሊት ሚሳዬል ሞኮረች


ሰሜን ኮሪያ የሚሳዬል ሙከራ። ፋይል - (Photo: REUTERS/Kim Hong-Ji/File Photo)
ሰሜን ኮሪያ የሚሳዬል ሙከራ። ፋይል - (Photo: REUTERS/Kim Hong-Ji/File Photo)

ሰሜን ኮሪያ ያታለመደ የምሽት ሚሳዬል ሙከራ ዛሬ አድርጋለች። ሙከራውን ያደረገችው በሠራተኞች ፓርቲ ምሥረታ ዓመታዊ በዓል ዋዜማ እና የአሜሪካ አውሮፕላን ጫኝ መርከብ ግብረሃይል የሁለት ሣምንት ወታደራዊ ልምምዱን ባጠናቀቀ ከሰዓታት በኋላ ነው።

አውሮፕላን ጫኝ መርከቡ ወደ ኮሬያ ባህረ ገብ ምድር ተመልሶ ያቀናው ሰሜን ኮሪያ መካከለኛ ርቀት ያለው ሚሳዬል በጃፓን አናት ላይ ማክሰኞ ዕለት ካስወነጨፈች በኋላ ነው።

ዛሬ እሁድ በውድቅት ሌሊት ሁለት የአጭር ርቀት ሚሳዬሎች ሙንቾን ተብሎ ከሚጠራው ቦታ፣ ወደ “ምሥራቅ ባህር” ወይም የ”ጃፓን ባህር” ተብሎ ወደሚጠራው የውሃ አካል ተወንጭፈዋል ሲል የደቡብ ኮሪያ ሠራዊት አስታውቋል። የጃፓኑ ተቀዳሚ ምክትል መከላከያ ምኒስትር ቶሺሮ ኢኖ ይህንኑ አረጋግጠው፣ የ”ጃፓን የተለየ የኢኮኖሚ ቀጠና” ተብሎ ከሚጠራው ክልል ወጣ ብሎ ባለ የውሃ አካላ ላይ ማረፉን አስታውቀዋል።

የቪኦኤዋ ዩኒስ ኪም ከሶል እንደዘገበችው፣ የዩናይትድ ስቴትስ ኢንዶ ፓሲፊክ የተባለው ወታደራዊ ዕዝ ሁኔታውን ከገመገመ በኋላ “የሚሳዬል ሙከራው በአሜሪካም ሆነ በአጋሮቿ ላይ የፈጠረው ስጋት የለም፤ ዩናይትድ ስቴትስ ደቡብ ኮሪያንና ጃፓንን እንደምትከላከል በድጋሚ እናረጋግጣለን” ብሏል።

XS
SM
MD
LG