በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አሜሪካ አጋሮቿን ከሰሜን ኮሪያ ጥቃት እንደምትከላከል በድጋሚ አስታወቀች


FILE - A missile that analysts believe could be the North Korean Hwasong-12 is paraded in North Korea on April 15, 2017. Japanese Defense Minister Yasukazu Hamada said a missile North Korea fired over Japan on Tuesday could have been a Hwasong-12. (AP)
FILE - A missile that analysts believe could be the North Korean Hwasong-12 is paraded in North Korea on April 15, 2017. Japanese Defense Minister Yasukazu Hamada said a missile North Korea fired over Japan on Tuesday could have been a Hwasong-12. (AP)

ሰሜን ኮሪያ መካከለኛ ርቀት ባሊስቲክ ሚሳዬል ትናንት በጃፓን አናት ላይ ማስፈንጠሯን ዩናይትድ ስቴትስ አውግዛ፣ አጋሮቿ የሆኑትን ደቡብ ኮሪያንና ጃፓንን እንደምትከላከል ቃል ገብታለች። ይህም ሆኖ የባይደን አስተዳደር ከፒዮንግያንግ ጋር ለመነጋገር አሁንም በሩ ክፍት መሆኑን አስታውቋል።

ለሰሜን ኮሪያ ሚሳዬል ተኩስ ምላሽ፣ የአሜሪካና የደቡብ ኮሪያ የአየር ሃይል አውሮፕላኖች ትናንት ማክሰኞ የጋራ ልምምድ ማድረጋቸውን የዋይት ሃውስ ቃል አቀባይ ካሪን ዣን-ፒየር አረጋግጠዋል።

“በጋራ የመከላከል ብቃታችንንና፣ በቅጽበት ተለዋዋጭ የሆነ ጥቃት የማድረስ አቅማችንን ለማሳየት፤ በሁለትዮሽም ሆነ በሶስትዮሽ በምናደርገው ግኑኝነት እንዲሁም ከኮሪያ ሪፐብሊክና ከዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ጋር በመሆን አስቸኳይና ዘላቂ መፍትሄ የምንሰጥበትን ሁኔታ ማቀናጀታችንን እንቀጥላለን” ብለዋል ዣን-ፒየር።

ሰሜን ኮሪያ ትናንት በጃፓን አናት ላይ ያስወነጨፈችው መካከለኛ ርቀት ባሊስቲክ ሚሳዬል በቅርቡ በወታደራዊ ሰልፍ ላይ ያሳየችውና፣ አዲስ ዓይነት ሊሆን እንደሚችል ታምኗል።

ከሌሎቹ ሚሳዬሎች በበለጠ 4ሺህ 600 ርቀት መጓዝ ሲችል፣ ወደ ሰማይ በመተኮስ ፈንታ፣ ወደ ጎን በጃፓን እናት ላይ አስፈንጥራዋለች ሰሜን ኮሪያ። ከ2017 ወዲህ ወደ ጃፓን አቅጣጫ ሲተኮስ የመጀመሪያው ነው።

የጃፓኑ ጠቅላይ ምኒስትር ፉሚዮ ኪሺዳ “በቅርቡ መልስ እንሰጥበታለን” ሲሉ ዝተዋል።

ታዛቢዎች እንደሚሉት ሰሜን ኮሪያ ሙከራውን ያደረገችው፣ በአሜሪካና በደቡብ ኮሪያ መካከል ከፍተኛ የባህር ላይ የጋራ ልምምድ ለማድረጋቸው መልስ ነው። ሃይልን ለመፈታተሸ ይመስላል፣ ዩ.ኤስ.ኤስ. ሮናልድ ሬገን የተሰኘው የአሜሪካው አውሮፕላን ጫኝ መርከብ ባለፈው ወር ወደ ደቡብ ኮሪያ ተጠግቶ ቆሟል።

የባይደን አስተዳድር አጋሮችን እንደሚከላከል ቢያሳውቅም፣ ከፒዮንግያንግ ጋር ለመነጋገር አሁንም በሩ ክፍት ነው ብሏል።

“ዓላማችን አሁንም የኮሪያን ባህረ-ገብ ምድር ከኑክሌር ነጻ ማድረግ ነው። ለዚህም ተጨባጭ እመርታ ላማሳየት፣ ቀጣይነት ያለውና እውነተኛ የሆነ የዲፕሎማሲ ድርድር ለማድረግ አሁንም ዝግጁ ነን። ከሰሜን ኮሪያ ጋር ካለምንም ቅድመ ሁኔታ ለመገናኘት ሁሌም ዝግጁ ነን” ሲሉ ተናግረዋል ዣን ፒየር።

በተመድ የአሜሪካ አምባሳደር፣ የጸጥታ ም/ቤቱ ፒዮንግያንግ ጅምላ ጨራሽ መሣሪያ ማምረቷን ለመግታት ስብሰባ እንዲደረግ ጠይቀዋል።

XS
SM
MD
LG