በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የቢሾፍቱው የእሬቻ በዓል


የቢሾፍቱው የእሬቻ በዓል
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:04 0:00

በርካቶች ባለፈው ቅዳሜ አዲስ አበባ ላይ የተከበረውን የእሬቻ በዓል ካከበሩ በኋላ ወደ ቢሾፍቱ ያቀኑትን ጨምሮ ቁጥራቸው የበዙ ታዳሚዎች ተገኝተዋል።

ከዋናዉ የፍጥነት መንገድ ወደ ከተማዋ የሚወስዱ አዉራ ጎዳናዎች በፀጥታ ኃይሎች ለሕዝብ ተሽከርካሪዎች ዝግ መደረጋቸው እንዳገላታቸዉ ከአዲስ አበባ በቀጥታ የመጡ አንዳንድ ተሳታፊዎች ተናግረዋል።

በሌላ በኩል የእሬቻ በዓል ትናንት እሁድ በዋሽንግተን ዲሲ እና በአካባቢው ነዋሪ የሆኑ የኦሮሞ ተወላጆች እና እንዲሁም ሌሎች ከአንዳንድ የዩናይትድ ስቴትስ ግዛቶች እና ከካናዳ በተሰባሰቡ ተሳታፊዎች ተከብሯል።

የበዓሉ ተሳታፊዎች መሃል ዋሽንግተን በሚገኘው የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ሊንከን መታሰቢያ ኃውልት ማዶ ካለው እና /Reflection Pool/ በሚል መጠሪያ ከሚታወቀው ግዙፍ ገንዳ አቅራቢያ የምስጋና ሥነ ሥርዓት ማከናወናቸው ተዘግቧል።

[ሙሉውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ያገኛሉ]

XS
SM
MD
LG