በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሰሜን ኮሪያ ተጨማሪ ሚሳይሎች አስወነጨፈች

A TV screen showing a news report about North Korea's missile launch with file footage is seen at the Seoul Railway Station in Seoul, South Korea, Oct. 1, 2022. On Saturday, North Korea fired two short-range ballistic missiles. (AP Photo/Lee Jin-man)

ሰሜን ኮሪያ ዛሬ ቅዳሜ ሁለት ባሊስቲክ ሚሳኤሎችን ወደ ባህር አስወንጭፋለች። የአሜሪካ ባላንጣዋ ሰሜን ኮሪያ በያዝነው ዓመት ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሚሳኤል አስወንጭፋለች። በዚህ ሳምንት ብቻ ሰባት መሆኑ ነው።

የዩናይትድ ስቴትስ ምክትል ፕሬዝደንት ካመላ ሃሪስ ባለፈው ሳምንት ጉብኝት ከማድረጋቸው ጥቂት ቀደም ብሉም እንድ ሚሳኤል ለቃለች ሰሜን ኮሪያ። ካመላ ሃሪስ “ግልጽ ጸብ አጫሪነት ነው” ብለውታል።

በሁለቱ ኮሪያዎች መካከል የሚገኘውንና ከወታደራዊ ሃይል ነጻ የሆነውን ቀጠና በጎበኙበት ወቅት፣ ሰሜን ኮሪያን “ጨካኝ ፈላጭ ቆራጭ” ገልጸዋታል ካመላ ሃሪስ።

ቶኪዮ ላይ ዛሬ የተናገሩት የጃፓን ምክትል የመከላከያ ምኒስትር ቶሺሮ ኢኖ፣ የሰሜን ኮሪያን ድርጊት በጽኑ አውግዘዋል። “የጃፓንን ብቻ ሳይሆን፣ የቀጠናውንና የዓለም አቀፉን ማህበረሰብ የሚያሰጋ ድርጊት ነው” ብለውታል።

ከያዝነው የፈረንጆት ዓመት ጅምሮ ሰሜን ኮሪያ 38 ባሊስቲክ ሚሴሎችን አስወንጭፋለች።

XS
SM
MD
LG