በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በቆጵሮስ ጉዳይ የቱርክና የግሪክ ፍጥጫ ተካሯል

FILE - Turkish Cypriot leader Ersin Tatar, stands on a military vehicle, right, as he reviews the military parade marking the 48th anniversary of the 1974 Turkish invasion in the Turkish occupied area of the divided capital Nicosia, Cyprus, July 20, 2022.

በግሪክና በቱርክ መካከል ለሁለት ተካፍለዋት ባለችው የቆጵሮስ ደሴት ጉዳይ ያለው ውጥረት ሰሞኑን እንደገና ከረር ብሏል።

በግሪክ ቆጵሮስ አስተዳደር ላይ የተጣለውን የጦር መሣሪያ ማዕቀብ አሜሪካ ማንሳቷን ምክንያት በማድረግ፣ ቱርክ በደሴቲቱ ላይ ያላትን ወታደራዊ እንቅስቃሴ መጨመሯን ትናገራለች።

አሜሪካ ከግሪክ ጋር ወግናለች ሲሉ የቱርክ የውጪ ጉዳይ ምኒስትር ይወነጅላሉ።

የቪኦኤው ዶሬይን ጆነስ ከኢስታንቡል እንደዘገበው፣ የውጪ ጉዳይ ምኒስትሩ ማቭሉት ቻቡሾሎ እንዳሉት፣ የቆጵሮስ ንትርክ ጉዳይን በተመለከተ “ዩናይትድ ስቴትስ የአቴንስ መጫወቻ አሻንጉሊት ሆናለች” ሲሉ ወቅሰዋል።

“ግሪኮቹን ለማስደሰት ሲባል እንድ ግዜ ከእነርሱ ጎን ከተቆመ በኋላ፣ ከእኛ ዘንድ ወዳጅነት መጠበቅ የለበትም፤ ለእንዲህ አይነቱ ነገር ቱርክ አትንበረከክም” ሲሉ ተደምጠዋል የውጪ ጉዳይ ምኒስትሩ።

በሜዲትሬኒያን ባህር ላይ የምትገኘው ቆጵሮስ ደሴት በእ.አ.አ. 1974 ዓ/ም ግሪክና ቱርክ ተካፍለዋታል። ግሪክ የአንበሳውን ድርሻ ቆርሳለች - ሁለት ሶስተኛውን። ያም ብቻ አይደለም - ዓለም አቀፍ የመንግስት እውቅና እስከ አሁን የተሰጠው ለግሪክ ቆጵሮስ አስተዳደር ብቻ ነው።

XS
SM
MD
LG