በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በሰሜን ወሎ ውጊያ ተባብሶ መቀጠሉን ነዋሪዎች ገለጹ


በሰሜን ወሎ ውጊያ ተባብሶ መቀጠሉን ነዋሪዎች ገለጹ
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:56 0:00

በአማራ ክልል የሰሜን ወሎ ዞን አካባቢዎች በዛሬው ዕለት ውጊያ መባባሱን የአካባቢው ነዋሪዎች ገለጹ። ለአሜሪካ ድምጽ አስያየታቸውን የሰጡ የአካባቢው ነዋሪዎች፣ ባለፈው ሳምንት ውስጥ አንድ ጊዜ ጠንከር ፣ሌላ ጊዜ ደግሞ ቀዝቀዝ እያለ ውጊያ መቀጠሉን ተናግረዋል፡፡ በዛሬው ዕለት ደግሞ በራያ ግምባር ጎብዬ አካባቢ ከባድ ውጊያ በመካሔድ ላይ መሆኑን አስተያየት ሰጪዎች ተናግረዋል፡፡ በስፍራው ያለውን ውጊያ በተመለከተ ከመንግስትም ይሁን ከሕወሃት ወገን የተባለ ነገር የለም፡፡

በአማራ ክልል የሰሜን ወሎ ዞን አካባቢዎች በዛሬው ዕለት ውጊያ መባባሱን የአካባቢው ነዋሪዎች ገለጹ።

ለአሜሪካ ድምጽ አስያየታቸውን የሰጡ የአካባቢው ነዋሪዎች፣ ባለፈው ሳምንት ውስጥ አንድ ጊዜ ጠንከር ፣ሌላ ጊዜ ደግሞ ቀዝቀዝ እያለ ውጊያ መቀጠሉን ተናግረዋል፡፡ በዛሬው ዕለት ደግሞ በራያ ግምባር ጎብዬ አካባቢ ከባድ ውጊያ በመካሔድ ላይ መሆኑን አስተያየት ሰጪዎች ተናግረዋል፡፡
በስፍራው ያለውን ውጊያ በተመለከተ ከመንግስትም ይሁን ከሕወሃት ወገን የተባለ ነገር የለም፡፡

በተያያዘ ዜና፣ ኤርትራ የትግራይ ክልልን ለመውጋት በአፋር ክልል በበረሃሌ በኩል አምስት ክፍለ ጦር ማሰለፏን በትዊተር ገጻቸው ያሰፈሩት የሕወሃት ቃል አቀባይ አቶ ጌታቸው ረዳ፣ በዚህ አቅጣጫ "ተሰልፏል" ያሉትን የኤርትራ ጦር የህወሓት ኃይሎች አምክነዋል ብለዋል፡፡

ይህን የአቶ ጌታቸውን ውንጀላ አስመልክቶ ከኤርትራም ይሁን ከኢትዮጵያ መንግስት በኩል እስካሁን የተሰጠ ምላሽ የለም፡፡

XS
SM
MD
LG