በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሩሲያው ላቭሮቭ በዩክሬን እየተካሄደ ያለውን የራስን እድል የመወሰን ምርጫን የተቃወሙ ምዕራባዊያንን አጣጣሉ


በማሪፖል የተቋቋመ ተንቀሳቃሽ የምርጫ ጣቢያ ዩክሬናዊያን ሲመርጡ
በማሪፖል የተቋቋመ ተንቀሳቃሽ የምርጫ ጣቢያ ዩክሬናዊያን ሲመርጡ

የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሩሲያ የዪክሬንን ክልሎች የአለም አቀፍ ስምምነቶችን በጣሰ መልኩ በሪፈረንደም ልትወስድ ነው በሚል በምዕራባዊያን የተነሳባቸውን ውግዘት አጣጣሉ።

ላቭሮቭ ትላንት ቅዳሜ በተባበሩት መንግስታት አጠቃላይ ጉባዔ ላይ ለጋዜጠኞች በሰጡት ቃል “የተመለከትነው እብደት የተሞላበት ሽብር ሁኔውን አሳባቂ ነው” ብለዋል።

በሉሃንስክ፣ በኬኼርሶን እና በከፊል የሩሲያ ቁጥጥር ስር ባሉ ዛፖሪዢያ እና ዶኔትስክ ክልሎች ላይ አርብ ዕለት የተጀመረው ምርጫ እስከ መጪው ማክሰኞ ድረስ ይቀጥላል። በሩሲያ የስደተኞች ጣቢያ ያሉ እና ከተጠቀሱት አካባቢዎች የመጡ ስደተኞችም እንዲመርጡ በሩሲያ የምርጫ ጣቢያዎች ተቋቁመዋል።

ይሁን እንጂ በዩክሬን ያሉ የአካባቢው ባለስልጣናት መራጮች ማስፈራራት እና ውክቢያ እየደረሰባቸው ነው ብለዋል።

ኪየቭ እና ምዕራባዊያን ይሄ የራስን ዕድል በራስ የመወሰን ምርጫ ሩሲያ የዓለም አቀፉን ሕግ በጣሰ መልኩ ቦታዎቹን የራሷ ግዛቶች ላይ ለመጨመር የምታደርገው ጥረት ነው እያሉ ነው።

ላቭሮቭ በበኩላቸው “ፕሬዘዳንት ፑቲን እንዳሉት የዴሞክራሲያዊ ሂደቱን ውጤት እናከብራለን” ብለዋል።

ይሁን እንጂ ዩክሬን በመጪው ማክሰኞ የሁኔታውን መቀጣጠል በተመለከተ የተ.መ.ድ የጸጥታ ምክር ቤት በጉዳዩ ላይ እንዲመክሩበት የጠራች ሲሆን ሩሲያ የዩክሬንን ግዛቶችን በቁጥጥሯ ስር ማዋሏን እንደማትቀበል አስታውቃለች።

ይህ የራስን ዕድል የመወሰን ምርጫ ዩክሬን በሰሜን ምስራቅ የሃገሪቱ ክፍል ባደረገችው ጥቃት ከሩሲያ ሰፊ ቦታዎች መልሳ ከተቆጣጠረች በኋላ በአስቸኳይ የተደረገ ነው። ምዕራባዊያን ሩሲያ የዩክሬንን አራት ክልሎች ግዛቷ አድርጋ በማጠቃለል ከዚህ በኋላ በእነዚህ ግዛቶች የሚደረጉ ጦርነቶችን በግዛቴ ላይ የተደረጉ ናቸው በማለት የኑክሌር ጥቃት ልታደርስ ትችላለች ሲሉ ስጋት ይዟቸዋል።

XS
SM
MD
LG