በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ጣሊያናዊያን ቀኝ ዘመም ፖለቲከኛን ወደ ስልጣን ሊያመጣ የሚችለውን ምርጫ ሲመርጡ ዋሉ


ጣሊያናዊያን በምርጫ ላይ እ.ኤ.አ 2022
ጣሊያናዊያን በምርጫ ላይ እ.ኤ.አ 2022

ጣሊያናዊያን የዩክሬኑ ጦርነት በተቀጣጠለበት፣ የሃይል አቅርቦት ዋጋ በጨመረበት እና ምዕራባዊያን የሩሲያን ጥቃት በአንድነት ለመፍታት እየተፈተኑ ባለበት ወቅት፤ ዛሬ እሁድ ምርጫ ሲያደርጉ ውለዋል። የዛሬው ምርጫ ውጤትም የሃገሪቱን ፖለቲካ ቀኝ ዘመም ያደርገዋል ተብሎ እየተጠበቀ ነው።

እሁድ ዕለት ከጠዋቱ 1 ሰዓት አንስቶ ምርጫው የተጀመረ ሲሆን እስከ እኩለ ቀን ድረስ በተካሄደው ምርጫ እ.ኤ.አ 2018 ምርጫ ጋር ተመሳሳይ ቁጥር ያለው ህዝብ እየመረጠ እንደነበር ታውቋል።

ምንም እንኳን ከምርጫው ጋር የተያያዙ አስተያየቶች ከ2 ሳምንት በፊት ጀምሮ እንዳይታተሙ ቢታገዱም ከዛ በፊት የታተሙ ጽሁፎች ግን የአዲሱ ትውልድ ፋሺስት የሆኑትን ቀኝ ዘመም ፖለቲከኛ ጆርጂ ሜሎኒ እና ወንድሞቻቸው ሰፊ የሆነ ተቀባይነት እንዳላቸው አመላክተዋል። ከሁለተኛው የአለም ጦርነት በኋላ ጣሊያናዊያን ቀኝ ዘመም ሲሆኑ ይሄ የመጀመሪያቸው ነው።

ጆርጂ ሚሎኒን የለዘብተኛ ግራ ዘመም ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ አባል የሆኑት የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስተር ኤንሪኮ ሌታ ይከተሏቸዋል።

ሜሎኒ ዛሬ ጠዋት በትዊተር ገጻቸው ላይ ባሰፈሩት መልዕክት “ዛሬ ታሪክ እንዲጻፍ ታግዛላቹ” ብለዋል። በአንጻሩ ተቀናቃኛቸው ሌታ በትዊተር ገጻቸው ላይ ምርጫ ሲመጡ ከሚያሳይ ፎቶ ጋር አያይዘው “መልካም ምርጫ” ሲሉ ተመኝተዋል።

XS
SM
MD
LG