በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሚኒስትሮች ግብረሃይል “ህወሓት በአማራ እና በአፋር ክልሎች ያደረሰውን ሰብዓዊ ጉዳት አረጋገጥኩ” አለ


የሚኒስትሮች ግብረሃይል “ህወሓት በአማራ እና በአፋር ክልሎች ያደረሰውን ሰብዓዊ ጉዳት አረጋገጥኩ” አለ
please wait

No media source currently available

0:00 0:08:54 0:00

ባለፈው ዓመት ህወሓት በገባባቸው የአማራና የአፋር አካባቢዎች “ሰዎች ከሕግ ውጭ እንደተገደሉ” የሚኒስትሮች ግብረሃይል አስታወቀ ግድያው በአብዛኛው በህወሓት ኃይሎችና በተወሰነ መልኩ ደግሞ ባለሥልጣናቱ “ሸኔ” በሚሉት ቡድን መፈፀሙን ግብረሃይሉ በምርመራ እንዳረጋገጠ አመልክቷል፡፡

በተጨማሪም ከ2ሺህ 200 በላይ ሴቶች “በህወሓት ኃይሎች ተደፍረዋል” የሚለው የሚኒስትሮች ግብረሃይል ከደህንነት ጋር በተያያዘ ትግራይ ክልል ውስጥ የተፈፀሙ ጥሰቶችን ግን እንዳልመረመረ ገልጿል፡፡

በኢሰመኮና በተመድ የሰብዓዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽነር ቢሮ የጣምራ ምርመራ ቡድን ምክረ ኃሳብ መሠረት የተቋቋመው ይህ ግብረሃይል በንብረት ላይም ከፍተኛ ውድመትና ዘረፋ መደረሱን አስታውቋል፡፡

አምነስቲ ኢንተርናሽናልም ባለፈው የካቲት ባወጣው ሪፖርት ህወሓት በአማራ ክልል ጭናና ቆቦ አካባቢዎች የተለያዩ ኢሰብዓዊ ተግባራትን መፈፀሙን መግለፁ ይታወሳል፡፡ ይሁን እንጂ ህወሓት የአምነስቲንም ይሁን በተመድና በኢሰመኮ የወጣውን የምርመራ ሪፖርት አልተቀበለም፡፡

በሌላ በኩል የተመድ የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት ባለሙያዎች ቡድን ባለፈው ሰኞ ያወጣውን ሪፖርት እራሱን ከሚመለከቱት በስተቀር በአብዛኛው እንደሚቀበል ህወሓት ገልጿል፡፡ በዛሬ የሚኒስትሮች ግብረሃይል ሪፖርት ላይ ግን እስካሁን ከመቀሌ የተሰማ ምላሽም ይሁን አስተያየት የለም።

የኢትዮጵያ መንግሥት ግን ሪፖርቱን ያጣጣለ ሲሆን የሚኒስትሮች ግብረሃይሉም ትናንት በሰጠው መግለጫ ሪፖርቱ “የፖለቲካ አጀንዳ ያነገበ ነው” ብሏል።

XS
SM
MD
LG