በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኢትዮጵያ መንግሥት የሰሞኑን የመንግሥታቱን ድርጅት ቡድን ሪፖርት ተቀባይነት የሌለው ሲል ተቸ


የኢትዮጵያ መንግሥት የሰሞኑን የመንግሥታቱን ድርጅት ቡድን ሪፖርት ተቀባይነት የሌለው ሲል ተቸ
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:25 0:00

በጄኔቫ የሚገኘው የተባበሩት መንግሥታት የሰብአዊ ምክር ቤት በኢትዮጵያ ጉዳይ ያቋቋመው የባለሞያዎች ቡድን ከትናንት በስቲያ ሰኞ በሰሜን ኢትዮጵያ ጉዳይ አዲስ ሪፖርት አውጥቷል።

"ዳግም ጦርነት ባገረሸባት ኢትዮጵያ ተጨማሪ የጭካኔ ድርጊት ሊፈጸም ይችላል" ሲል ያስጠነቀቀው የቡድኑ ዘገባ በግጭቱ ያሉ ወገኖች የጦር ወንጀል ስለመፈጸማቸው እና የሰብአዊ መብት ስለመጣሱ አሳማኝ ምክኒያት አለ ብሏል።

ሪፖርቱ አክሎም ቡድኑ "በትግራይ ክልል በኢትዮጵያ መንግሥት እና በአጋሮቹ ዘጠና በመቶውን ሕዝብ ለከፋ ችግር የዳረገ በስብዕና ላይ የተፈጸመ ወንጀል ስለመኖሩ አሳማኝ ምክኒያት አለ ከሚል ድምዳሜ ላይ ደርሷል” ይላል።

ሪፖርቱን አስመልክቶ የኢትዮጵያ መንግሥት በሰጠው ምላሽ "ቀደም ሲል ጦርነቱን የጀመረው እና አሁንም የሰብአዊ ረድኤቱን ሥራ በማደናቀፍ አዲስ ጦርነት የክፈተውን ኃይል ተጠያቂ ማድረግ ያልፈቀደ ውሳኔ" ሲል ሪፖርቱን ያወጣውን ቡድን ወቅሷል።

XS
SM
MD
LG