በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት እና የዩናይትድ ስቴትስ የሰላም ጥረት


የሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት እና የዩናይትድ ስቴትስ የሰላም ጥረት
please wait

No media source currently available

0:00 0:09:32 0:00

የሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት ተባብሶ በቀጠለበት በዚህ ጊዜ፣ ህወሓት ለትግራይ ህዝብ የክተት ጥሪ አቅርቧል።

“ከማንኛውም ጊዜ በላይ የእያንዳንዱን ትግራዋይ ተሳትፎ የሚጠይቅ የህለውና ፈተና ገጥሞናል” ያለው የትግራይ ክልል መንግሥት ማዕከላዊ ኮማንድ፣ በተባለ አካል የወጣው መግለጫ “የጠላቶቻችንን ህልም ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ ለማምከን እያደረግን ባለው ጦርነት ሙሉ በሙሉ እንድትከት” በማለት ነው ጥሪውን ያቀረበው ።

ከኢትዮጵያ መንግሥት በኩል እስካሁን የቀረበ ተመሳሳይ የክተት ጥሪ የለም፡፡ ለህወሓት ክስ ምላሽ ከመስጠት የተቆጠበው የኢትዮጵያ መንግስት፣ ሕወሓት “ሕዝባዊ ማዕበል” የጦርነት ስልትን እንደሚከተል በመግለጽ በተደጋጋሚ መወንጀሉ ይታወሳል፡፡

ለጦርነቱ ዳግም መቀስቀስም ሁለቱም ወገኖች ጣታቸውን መቀሳሰራቸውን ቀጥለዋል፡፡

የዩናይትድ ስቴትስ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ ልዑክ ማይክ ሀመር መሠረታዊ አገልግሎቶች እንደገና ካልተጀመሩ ወደ ጦርነት ለመግባት እየተዘጋጁ እንደነበር የትግራይ ባለሥልጣናት በጣም ግልጽ አድርገው ነበር በማለት አስታውሰዋል።

ይሄንን መነሻ ያደረጉት የኤርትራ ማስታወቂያ ሚኒስትር የማነ ገብረመስቀል፣ “የዩናይትድ ሰቴትሱ ልዩ ልዑክ ህወሓት ጦርነት ለመክፈት ማሰቡን ያውቁ እንደነበር ዘግይተው አምነዋል” በማለት “ይህ ደግሞ የተለያዩ ጥያቄዎችን ያስከትላል” ብለዋል።

ልዩ ልዑኩ ሀመር በበኩላቸው “የኤርትራ ወታደሮች ወደ ኢትዮጵያ ትግራይ ክልል እንደገቡ ሀገራቸው እንደምታውቅ ገልጸው አውግዘዋል።

በአገራቸው ላይ የሚሰነዘሩ ውንጀላዎችን በድጋሚ ያጣጣሉት የኤርትራ ማስታወቂያ ሚኒስትር ግን ዩናይትድ ስቴትስ እና ምዕራባውያን ሕወሓትን በተመለከተ ይዘውታል ያሉትን አቋም በጽኑ ተችተዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ የተመድ የሰብዓዊ መብቶች ባለሙያዎች ኮሚሽን ያወጣውን ሪፖርት የኢትዮጵያ መንግሥት አጣጥሏል፡፡

XS
SM
MD
LG