በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ቤኒሻንጉል ጉሙዝን መልሶ ለማቋቋም የሚያስፈልገው ርብርብ ጉዳይ



ቤኒሻንጉል ጉሙዝን መልሶ ለማቋቋም የሚያስፈልገው ርብርብ ጉዳይ
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:19 0:00

ቤኒሻንጉል ጉሙዝን መልሶ ለማቋቋም የሚያስፈልገው ርብርብ ጉዳይ

ባለፉት ሁለት ዓመታት ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ውስጥ በነበረው የጸጥታ ችግር የደረሰውን ጉዳት ለመቀልበስና እና መልሶ ለማቋቋም ከ38 ቢሊዮን ብር በላይ እንደሚያስፈልግ የክልሉ መንግሥት ገለጸ።

የክልሉ አደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ታረቀኝ ታሲሳ "በሦስት ዞኖችና አንድ ልዩ ወረዳ ውስጥ የወደሙ የተለያዩ መሰረተ ልማቶችን መልሶ ለመገንባትና ለማደስ ከሁለት እስከ አምስት ዓመት ይወስዳል” ካሉ በኋላ ለተግባራዊነቱም ህብረተሰቡ፣ መንግስትና የተለየዩ የግብረ ሰናይ ድርጅቶች በጋራ እንደሚሰሩ አስታውቀዋል።

ከክልሉ ተፈናቅለው ከነበሩ 475 ሺ ሰዎች መካከል እስከ አሁን ከ265 ሺ በላይ የሚሆኑ ወደየአካባቢያቸው ተመልሰዋል ሲሉ ኃላፊው ጨምረው ገልጸዋል።

በክልሉ የሚንቀሳቀሰው ቦሮ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ የተባለው ተፎካካሪ የፖለቲካ ድርጅት “በክልሉ ግጭት በነበረባቸው አካባቢዎች ለደረሰው ጉዳት የተሰጠው ትኩረት አናሳ ነው” ብሏል።

[ሙሉውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ያገኛሉ]

XS
SM
MD
LG