በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሰብዓዊ መብቶች ጉዳይ ለወጣቶች


የሰብዓዊ መብቶች ጉዳይ ለወጣቶች
please wait

No media source currently available

0:00 0:09:08 0:00

የሰብዓዊ መብቶች ጉዳይ ለወጣቶች

የመብቶችና ዴሞክራሲ ዕድገት ማዕከል ተቋም (ካርድ) ባሳለፍነው ሳምንት በአዲስ አበባ ሲሰጥ የቆየውን'የአዲሱ ትውልድ የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋቾች ሥልጠና' አጠናቋል፡፡

በስልጠናው ላይ የተሳተፉ ወጣቶች ከጋቢና ቪኦኤ ጋር ባደረጉት ቆይታ በስልጠናው ላይ በመማር ማስተማር ሂደት ውስጥ ከትምህርት ጥራት ጋር ተያይዘው የሚነሱ የመብት ጥሰቶችን እና በጸጥታ ማስከበር ስራ ላይ ከተሰማሩ የመንግስት አካላት ጋር የሚኖር ንግግር በተመለክተ መብት እና ግዴታዎቻቸውን ማወቃቸውን ገልጸዋል።

ከዚህ በተጨማሪም ወጣቶቹ ከዚህ ቀድም መብትን ለመጠየቅ ይሄዱበት የነበረው ጉልበት እና ሃይል የተቀላቀለበት አጠያየቅ እንዲሁም የሌሎችን መብት የጣሱ አካሄዶች ላይ ማስወገድ ላይ ግንዛቤ እንደወሰዱ ገልጸዋል።

ስልጠናው ለ10 ተከታታይ ሳምንታት የተካሄደ ሲሆን ከተለያዩ በአዲስ አበባ ከሚገኙ የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት የተውጣጡ 175 ተማሪዎች ተሳትፈውበታል። ስልጠናው ዘንድሮ ለሁለተኛ ጊዜ የተካሄደ መሆኑንና በቀጣይ ወደ ክልል ከተሞች እንደሚስፋፋም ተቋሙ አስታውቋል።

/ዝርዝሩን ከተያያዘው የምስል ፋይል ይከታተሉ/

XS
SM
MD
LG