በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሰላሙ እንቅፋት መተማመን አለመኖሩ ነው - አምባ. ሐመር


የሰላሙ እንቅፋት መተማመን አለመኖሩ ነው - አምባ. ሐመር
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:59 0:00

ሰላም እንዳይወርድ እያደረገ ያለው ዋና እንቅፋት “በኢትዮጵያ መንግሥትና በህወሓት መካከል መተማመን አለመኖሩ” መሆኑን የዩናይትድ ስቴትስ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ ልዑክ አምባሳደር ማይክ ሐመር አመልክተዋል።

ልዩ ልዑኩ የኢትዮጵያ ቆይታቸውን በማስመልከት ዛሬ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ከኢትዮጵያ መንግሥት ከፍተኛ ባለሥልጣናትና ከህወሓት መሪዎች ጋር መወያየታቸውን ተናግረዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ “ኤርትራ ሙሉ ጥቃት ከፍታብናለች” ሲሉ የህወሓት ቃል አቀባይ አቶ ጌታቸው ረዳ ዛሬ ባወጡት ትዊት ከስሰዋል፡፡ “የኢትዮጵያ ጦርም ከኤርትራ ኃይል ጋር ተሰልፎ ጥቃት እየፈፀመ እንደሆነ” በመግለፅ ወንጅለዋል።

ይሁን እንጂ ከኢትዮጵያም ሆነ ከኤርትራ መንግሥታት እስካሁን የተሰጠ ምላሽ የለም፡፡

በሌላ በኩል በሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት የተፈፀሙ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶችን እንዲመረምር በመንግሥታቱ ድርጅት የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት የተቋቋመው ዓለም አቀፍ መርማሪ ኮሚሽን ትናንት ባወጣው ሪፖርት “ጦርነቱ በ2013 ዓ.ም ከተጀመረ አንስቶ ሰፊ የመብቶች ጥሰቶች መፈፀማቸውን የሚያሳይ ማስረጃ ማግኘቱን” አስታውቋል፡፡

XS
SM
MD
LG