በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኢትዮጵያዊው ታዳጊ በዓለም አቀፍ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ውድድር ለሩብ ፍጻሜ ደረሰ


ኢትዮጵያዊው ታዳጊ በዓለም አቀፍ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ውድድር ለሩብ ፍጻሜ ደረሰ
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:59 0:00

ኢትዮጵያዊው ታዳጊ በዓለም አቀፍ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ውድድር ለሩብ ፍጻሜ ደረሰ

ከሰሞኑ አቤል ዳኜ የሠራው በቀላል ምሳሌ እና ቋንቋ በሁካታ መሃል ሆኖ ድምፅን ማጥፋት የሚቻልበት የቴክኖሎጂ ፈጠራ ጽንሰ ሃሳብ የሚያስረዳው ቪዲዮ በማኅበራዊ መገናኛ ብዙሃን ላይ መነጋገሪያ ሆኗል። ነዋሪነቱን በዩናይትድ ስቴትስ ያደረገው አቤል ዳኜ የ18 ዓመት ወጣት ሲሆን፣

“ብሬክስሩ፣ ጁኒየር ቻሌንጅ” በተሰኘ የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ እና ሂሳብ ውድድር ላይ ከ2400 ሰዎች መካከል ለዕሩብ ፍጻሜ ከደረሱ 30 ሰዎች አንዱ መሆን ችሏል።

“ኮምፒውተር ሳይንስ ፍቅሬን ያዳበርኩት ከአባቴ ነው” የሚለው አቤል የወደፊት ፍላጎቱም ትምህርቱን ጨርሶ ኢትዮጵያን መርዳት እንደሆነ ይናገራል። በአሁኑ ክረምትም በደብረ ማርቆስ ሀዲስ ዓለማየሁ የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ለሚማሩ ከመቶ በላይ ለሚሆኑ ተማሪዎች ዌብ ግንባታ ሲያስተምር ቆይቷል።

አቤል ይህን “ብሬክስሩ” [Breakthrough] የተሰኘ ሽልማት ካሸነፈ የ250 ሺ ዶላር የነጻ የትምህርት ዕድል፣ 100 ሺ ዶላር ለተማረበት የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት የሳይንስ ቤተ-ሙከራ ግንባታ እና እሱን ላበረታታ እና ላነቃቃ መምህር የ50 ሺህ ዶላር ሽልማት የሚያገኝ ይሆናል። ነገር ግን ይሄ ይሆን ዘንድ “ብሬክስሩ ቻሌንጅ” የፌስቡክ እና የዩቱብ ገጽ ላይ ሰዎች ላይክ፣ ኮሜንት በማድረግ እንዲያግዙት ጠይቋል።

አቤል ዳኜ እና ወላጅ አባቱ ዶ/ር አሰፋ ዳኜ ከአሜሪካ ድምፅ ጋር ቆይታ አድርገዋል።

/ዝርዝሩን ከተያያዘው የምስል ፋይል ይከታተሉ/

XS
SM
MD
LG