በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ባይደን ለንግስቲቱ ቀብር ለንደን ገብተዋል


President Joe Biden and first lady Jill Biden (right) view the coffin of Queen Elizabeth II, lying in state on the catafalque in Westminster Hall in London, Sept. 18, 2022.
President Joe Biden and first lady Jill Biden (right) view the coffin of Queen Elizabeth II, lying in state on the catafalque in Westminster Hall in London, Sept. 18, 2022.

በመቶ የሚቆጠሩ የዓለም መሪዎች በነገው ዕለት በሚፈጸመው የእንግሊዟ ንግስት ዳግማዊት ኤልሳቤጥ የቀብር ስነ ሥርዓት ላይ ለመገኘነት ለንደን ላይ ተሰባስበዋል።

የአሜሪካው ፕሬዝደንት ጆ ባይደንና ባለቤታቸው ጅል ባይደን ትናንት ቅዳሜ ለንደን መግባታቸው ታውቋል።

የቪኦኤዋ አኒታ ፓወል ከለንደን እንደዘገበቸው፣ በማዕከላዊ ለንደን በርካቶች ሲሰባሰቡ፣ የዓለም መሪዎች ደግሞ ላንካስተር ሃውስ ወደተባለው የውጪ ጉዳይና የጋራ ብልጽግና ቢሮ አምርተው ከሳምንት በፊት በ96 ዓመታቸው ህይወታቸው ላለፈው ዳግማዊት ኤልሳቤጥ ሃዘናቸውን ገልጸዋል።

ባይደንና ባለቤታቸው በዌስትሚኒስተር አዳራሽ በመገኘት ካለፈው ረቡዕ ጀምሮ በክብር ያረፈውን የንግስቲቱን አስከሬን የተመለከቱ ሲሆን፣ ንጉስ ቻርለስ ሶስተኛ ለእንግዶቻቸው የአቀባበል ስነ ሥርዓት እንደሚያደርጉም የጠበቃል።

የእንግሊዝ ዘውድ፣ በንግስቲቱ የቀብር ስነ ሥር ዓት ላይ እንዲገኙ ለሳውዲ አረቢያው አልጋ ወራሽ ሞሃመድ ቢን ሳልማን ጥሪ በማድረጉ ጭቅጭቅን ፈጥሯል። አልጋ ወራሹ ጋዜጠኛ ጅማል ካሾግጂን ጭካኔ በተሞላበት ሁኔታ አስገድለዋል የሚል ውንጀላ ይቀርብባቸዋል። ዘግይቶ በወጣ ሪፖርት ደግሞ ንጉሱ በቀብር ስነ ሥርዓቱ ላይ እንደማይገኙ ታውቋል።

የእንግሊዝ ዘውድ፣ የሩሲያ፣ ቤላሩስ፣ ሲሪያ፣ አፍጋኒስታን እና ቬንዝዌላን መሪዎች በቀብሩ ላይ እንዲገኙ አልጋበዘም።

XS
SM
MD
LG