በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ፑቲን በዩክሬን ላይ ጥቃት ለማጠናከር ዝተዋል፣ ህንድ እና ቻይናን አግባብተዋል


የሩሲያው ፕሬዚደንት ቭላድሚር ፑቲን ከቻይናው ፕሬዚደንት ሺ ጂንፒንግ ጋር ፣ በሻንጋይ የትብብር ድርጅት ጉባኤ ላይ
የሩሲያው ፕሬዚደንት ቭላድሚር ፑቲን ከቻይናው ፕሬዚደንት ሺ ጂንፒንግ ጋር ፣ በሻንጋይ የትብብር ድርጅት ጉባኤ ላይ

በዩክሬን የመልሶ ማጥቃት ዘመቻዎች ማግስት የሩሲያ ፕሬዚደንት ቭላድሚር ፑቲን ጥቃቶችን ለማጠናከር ዝተዋል። በትናንትናው ዕለት የዩክሬን ኃይሎች በሩሲያ መሰረተ-ልማቶች ላይ ጥቃት ማድረሳቸውን ካለቆሙ ሞስኮ በምላሹ በዩክሬን ወሳኝ መሰረተ-ልማቶች ላይ ጥቃቶችን እንደምታበረታ ፑቲን አስጠንቅቀዋል ።

ኡዝባኪስታን ውስጥ የነበረውን የየሻንጋይ ትብብር ድርጅት ጉባኤ ከታደሙ በኃላ፣ከዘጋቢዎች ጋር የተነጋገሩት ፑቲን ፣ የዩክሬንን ምስራቃዊ የዶንባስ ቀጠና ነጻ ማውጣት የሩሲያ ዋና የጦር ግብ እንደሆነ እና ሊከለስ እንደማይችልም አስተውቀዋል ።

ሞስኮ ወዶ ገብ ወታደሮችን ብቻ ወደ ዩክሬን ማዝመቷን ያነሱት ፑቲን “ በጥድፊያ ውስጥ አይደለንም"፣ ሲሉም ተሰምተዋል ።ለዘብተኛ-ያልሆኑ ፖለቲከኞች እና የጦር ጉዳይ ጦማሪያን ክረምሊን የዩክሬንን በመከተል ሰፊ የጦር አደረጃጀት በመተግበር የሩሲያን የሰው ኃይል እጥረት እንዲቀርፍ ጥሪ አቅርበዋል።

ከዩክሬን ፈጣን የመልሶ ማጥቃት ዘመቻ በኃላ ሩሲያ ከሰሜን ምስራቅ የየዩክሬን ስፍራዎች ኃይሏን ለማስወጣት እንደተገደደች ይታወሳል። በሩሲያ ተይዘው የነበሩ ከተሞች እና መንደሮችን ዩክሬን መልሳ መቆጣጠሯ ፣ በጦርነቱ መጀመሪያ የሩሲያ ጦር ከዋና ከተማዋ ኪቭ አቅራቢያ ካፈገፈገ ወዲህ፣ ግዙፉ የጦር ተግዳሮት ተደርጎ ተቆጥሯል።

በዩክሬን መልሶ ማጥቃት ዙሪያ የመጀመሪያ በሆነ አስተያየታቸው ፑቲን ጦርነቱ “ወዴት እንደሚያመራ እና በምን ሁኔታ እንደሚጠናቀቅ እንመልከት !” ብለዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ፑቲን ህንድ በዩክሬን ጦርነት ዙሪያ ያላትን ጭንቀት ለማርገብ ያላቸውን ፍላጎት አሳይተዋል። ፑቲን የህንዱን ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲን ሞስኮ ጦርነቱ በፍጥነት እንዲቆም እንደምትሻ ሆኖም ግን የዩክሬን ባለስልጣናት ለድርድር እንዳልተስማሙ ነግረዋቸዋል ።

የዩክሬኑ ፕሬዚደንት ቮሎድሜር ዘለንስኪ ሩሲያ የምር ድርድር ለማድረግ እንደማትሻ በመግለጽ ሲከሱ ሰንብተዋል። ንግግር ይጀመር ዘንድ የሩሲያ ወታደሮች ከተቆጣጠሯቸው ስፍራዎች በቅድሚያ መልቀቅ እንዳለባቸውም አሳስበዋል።ፑቲን ከሞዲ ጋር በነበራቸው ቆይታ የተናገሩት ፣ ሀሙስ ዕለት ከቻይናው ፕሬዚደንት ሺ ጂንፒንግ ጋር በነበራቸው ቆይታ የተናገሩትን በድጋሚ ያስተጋባ ነው። ፑቲን ዢን መንግስታቸው በዩክሬን ጉዳይ ለያዘው "ሚዛናዊ" አቋም አመስግነው ፣ ከጦርነቱ ጋር በተገናኘ ለቻይና "አሳሳቢ" የሆኑ ጉዳዮች ላይ ለመወያየት ዝግጁ እንደሆኑ ተናግረዋል።

ዘገባው የሶሼትድ ፕረስ ነው።

XS
SM
MD
LG