በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

 የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ትኩረት ላልተሰጣቸው ሰብዓዊ ርብርቦች የሚውል 100 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ ለቀቀ


መስሪያቤቱ ፣ በችግር ውስጥ ላሉ፣ ሆኖም ብዙ ትኩረት ላልተሰጣቸው ሀገራት የሚውል 250 ሚሊየን ዶላር እንደመደበም አስታውቋል።
መስሪያቤቱ ፣ በችግር ውስጥ ላሉ፣ ሆኖም ብዙ ትኩረት ላልተሰጣቸው ሀገራት የሚውል 250 ሚሊየን ዶላር እንደመደበም አስታውቋል።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የተቀናጀ የሰብዓዊ ተግባራት ጉዳዮች መስሪያ ቤት በምህጻሩ ኦቻ ፣ ተፈላጊውን ትኩረት ባላገኙ የአስቸኳይ ጊዜ ሁኔታዎች ውስጥ ናቸው ላላቸው በሚሊየኖች የሚቆጠሩ የዓለም ህዝቦች የሚውል 100 ሚሊየን ዶላር ፣ ከማዕከላዊ የአደጋ ጊዜ የገንዘብ ቋቱ እንደለቀቀ ይፋ አድርጓል።

ኦቻ ፣ በአፍሪካ ፣ እስያ ፣ አሜሪካዎች እና መካከለኛው ምስራቅ ውስጥ የሚገኙ 11 ሰብዓዊ እንቅስቃሴዎች ሀቅማቸው በመናመኑ ምክንያት፣በሚሊየኖች የሚቆጠሩ ሰዎች ህይወት ለአደጋ ተጋልጧል።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በመላ ዓለም ላይ በግጭቶች፣ የአየር ንብረት ለውጥ በፈጠራቸው ችግሮች ፣ ረሃብ እና መፈናቀል ስጋት ለተጋረጠባቸው 204 ሚሊየን ሰዎች የሚውል 49.5 ቢሊየን ዶላር እንደሚያስፈልገው አስታውቋል ።እስከአሁን የተገኘው ግን 17.6 ቢሊየን ብቻ መሆኑን የገለጹት የኦቻ ምክትል ቃል አቀባይ ጄንስ ላርኪ ቀሪው 32 ቢሊየን ክፈተት እስካሁን ከታዩት ሁሉ የሰፋው እንደሆነ ተናግራዋል።

ላርኪ አሁን ላይ የተለቀቀው 100 ሚሊየን ዶላር ፣ የመንን፣ ደቡብ ሱዳን ፣ ማይንማር እና ቪንዙዌላን ጨምሮ በ11 ሀገራት ውስጥ የሚገኙ ነፍስ አድን እንቅስቃሴዎችን ለማጠናከር ይውላል።

መስሪያቤቱ ፣ በዚህ ዓመት በችግር ውስጥ ላሉ፣ ሆኖም ብዙ ትኩረት ላልተሰጣቸው ሀገራት የሚውል 250 ሚሊየን ዶላር እንደመደበም አክለዋል ።

XS
SM
MD
LG