በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሰሜን ኢትዮጵያው ግጭት፣ የዋይት ሃውስ ደብዳቤ እና ሌሎች ርዕሶች


የሰሜን ኢትዮጵያው ግጭት፣ የዋይት ሃውስ ደብዳቤ እና ሌሎች ርዕሶች
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:21 0:00

የሰሜን ኢትዮጵያው ግጭት፣ የዋይት ሃውስ ደብዳቤ እና ሌሎች ርዕሶች

በመቀሌ በተፈጸመ የድሮን ጥቃት ሰላማዊ ሰዎች መገደላቸውን እና መቁሰላቸውን ህወሓት አስታወቀ።

ስለጥቃቱ መፈጸም በትዊተር ገጻቸው ያመለከቱት የህወሓት ቃል አቀባይ አቶ ጌታቸው ረዳ፣ በጥቃቱ ምን ያህል ሰዎች እንደተጎዱ ግን አልገለጹም፡፡

የኢትዮጵያ መንግሥት ለዚህኛው ክስም ምላሽ አልሰጠም፡፡ ይሁን እንጂ ከዚህ ቀደም የቀረቡ መሰል ክሶችን ማስተባበሉ ይታወቃል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ በፌዴራል መንግሥት እና በህወሓት ኃይሎች መካከል በመካሔድ ላይ ያለው የሰሜኑ ጦርነት አሁንም በተለያዩ ግምባሮች እንደቀጠለ መሆኑን የትግራይ ባለሥልጣናት በመግለጽ ላይ ናቸው፡፡

የኢትዮጵያ መንግሥት ከጦርነቱ ጋር በተያያዘ ላለፉት 2 ሳምንታት ያለው ነገር ባይኖርም፣ ጦርነቱ መቀጠሉን በሰሜን ወሎ የሚገኙ ነዋሪዎችም ለአሜሪካ ድምፅ አረጋግጠዋል፡፡

በተያያዘ ዜና፣ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ከሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት ጋር በተያያዘ ከዓመት በፊት ያወጁት ብሔራዊ የአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጅ እንዲራዘም ወስነዋል፡፡

[ሙሉውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ያገኛሉ]

XS
SM
MD
LG