የሱዳን አዋሳኝ በሆነው ምዕራብ ጎንደር ዞን መተማ ወረዳ በሕወአት ታጣቂዎች እና በመንግሥት ሃይሎች መካከል ከዛሬ ጠዋት አንስቶ ዉጊያ እየተካሄደ መሆኑን የአካባቢው ባለስልጣናት እና ነዋሪዎች ይናገራሉ። ባለስልጣናቱ እና ነዋሪዎቹ ሽንፋ በተባለው የመተማ ንዑስ ወረዳ ጥቃት የከፈተው ሕወአት ነው ሲሉ ወንጅለዋል።
ይሁንና ላሁኑ ውንጀላ ቀጥተኛ ምላሽ ያልሰጠው ሕወአት ቀደም ሲል የቀረቡ መሰል ውንጀላዎችን በማስተባበል የኢትዮጵያን መንግሥት በጥቃት ፈጻሚነት ይከሳል።
የሕወሓት ሊቀመንበር ዶ/ር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል አዲሱን ዓመት አስመልክተው ባስተላለፉት መልዕክት ወረራ እየተፈጸመብን ነው’ ሱሉ ወንጅለዋል።
በተያያዘ ዜና ሰሞኑን ጦርነት ሲካሄድባቸው በነበሩ አንዳንድ አካባቢዎች ያለው ውጊያም እንደቀጠለ መሆኑን የአሜሪካ ድምፅ ያነጋገራቸው ነዋሪዎች ጠቁመዋል።