በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሶማሊያ ጦር 20 መንደሮችን ከአል-ሸባብ “ነጻ” አውጥቼያለሁ አለ

FILE - A handout photo taken June 10, 2016, and released by AMISOM shows soldiers serving under the African Union Mission in Somalia (AMISOM) on foot patrol in Halgan village, Hiran region. Civilians in the region have been targetted by recent al-Shabab a

የሶማሊያ መከላከያ ሰራዊት በማዕከላዊ ሂራን ግዛት በእስላማዊው አክራሪ ቡድን አል-ሸባብ ተይዘው የነበሩ 20 መንደሮችን ማስለቀቁን አስታወቀ።

የሶማሊያ ብሄራዊ የጦር ሠራዊት አዛዥ የሆኑት ሻምበል ሞሃመድ ኢብራኢም ለቪኦኤው ሞሃመድ ዳይሴን በስልክ እንደነገሩት፣ የሰራዊቱ አባላት በአካባባው ካሉ የታጠቁ ነዋሪዎች ጋር በመተባበር ከመቶ በላይ የአል-ሸባብ ታጣቂዎችን ሲገድሉ 20 የሚሆኑ መንደሮችን ከአል -ቃይዳ ጋር ግንኙነት ካለው ቡድን ነጻ አውጥተናል ብለዋል።

እንደገና በቁጥጥር ስር ከዋሉት መደሮች ውስጥ፣ ከኢትዮጵያ ጋር የምትዋሰነው ፊዶው ከተማን ጨምሮ ሌሎችም በሂራን ግዛት የሚገኙ ስልታዊ ቦታዎች ይገኙባቸዋል ተብሏል።

አዛዡ አክለውም 20 የአል-ሸባብ ተዋጊዎች ተማርከዋል ብለዋል።

በዘመቻው ወቅት ጦራቸው ከአየር ዕርዳታ ማግኘቱን ነገር ግን ከየትኛው ሃገር እንደሆነ ከመግለጽ መቆጠባቸውን የሞሃመድ ዳይሴን ዘገባ አመልክቷል።

ዘመቻው እንደሚቀጥልና አሁንም በመካሄድ ላይ መሆኑን አዛዡ ተናግረዋል።

አል-ሸባብ የመንግስትን መግለጫ በተመለከተ አስተያየት ባይሰጥም፣ በሂራን ግዛት በሚገኙ የሶማሊያ የጸጥታ ሃይሎች ላይ ያነጣጠረ የቦምብ ጥቃት መፈጸሙን ገልጿል።

XS
SM
MD
LG