በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የቻይናውና የሩሲያው መሪ ሊገናኙ ነው 


FILE - President Vladimir Putin, right, and President Xi Jinping enter a hall for the talks in the Kremlin in Moscow, Russia, June 5, 2019.
FILE - President Vladimir Putin, right, and President Xi Jinping enter a hall for the talks in the Kremlin in Moscow, Russia, June 5, 2019.

የቻይናው ፕሬዝደንት ሺ ጂንፒንግ ከኮቪድ 19 ወረርሽኝ በኋላ ለመጀመሪያ ግዜ ወደ ውጪ ሀገር በመጓዝ ከሩሲያ አቻቸው ቭላድሚር ፑቲን ጋር ማዕከላዊ እሲያ ውስጥ እንደሚገናኙ ተነግሯል።

ፕሬዝደት ሺ በእ.አ.አ. 2013 ስልጣን ከተቆናጠጡ ጀምሮ ከፕሬዝደንት ፑቲን ጋር 38 ግዜ የተገናኙ ሲሆን፤ ከጆ ባይደን ጋር ግን የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝደንት ከሆኑ ወዲህ በአካል ተገናኝተው አያውቁም።

እንደ ሮይተርስ ዜና ወኪል ዘገባ ከሆነ፣ ሺ ወደ ውጪ ሀገር ሲሄዱ ከኮቪድ 19 ወረርሽን በኋላ የመጀመሪያ ግዜያቸው ሲሆን፣ ለሶስተኛ ዘመን በፕሬዝደንትነት በስልጣን ላይ ለመቆየታቸው እንዲሁም በዓለም የፖለቲካ መድረክ ሃያላን ሀገራት ፍትጊያ ላይ ባሉበት ሰዓት በያዙት የዓለም መሪነት ሚና የሚተማመኑ መሆናቸውን ያሳያል።

የቻይና ኮሚኒስት ፓርቲ በሚቀጥለው ወር ጉባኤውን የሚያካሂድ ሲሆን፣ ሺ ጂንፒንግ ለሶስተኛ የአምስት ዓመት ስልጣን እንደሚቀጥሉ ይጠበቃል። ይህም ከማኦ ዜዱንግ በኋላ ረጅምና ከፍተኛ ስልጣንን የተቆጣጠሩ የቻይና መሪ ያደርጋቸዋል።

በዩክሬን ጦርነት ምክንያት ሩሲያ ከምዕራቡ ዓለም ጋር ፍጥጫ ላይ ባለችበት፣ ከታይዋን ጋር ተያይዞ ያለው ቀውስ በተማሟቀበት እንዲሁም የዓለም ኢኮኖሚ በተቀዛቀዘበት ወቅት ሺ ጂንፒንግ ረቡዕ ለይፋዊ ጉብኝት ወደ ካዛክስታን ያመራሉ።

ከዛም ወደ ኡዝቤክስታን በማምራት በጥንታዊቷ ከተማ ሳማርካንድ በሚካሄደው የ”ሻንጋይ ትብብር ድርጅቶች ጉባኤ” ላይ ከሩሲያው ፕሬዝደንት ጋር ይገናኛሉ ሲሉ ክሬምሊንና ካዛክስታን አስታውቀዋል። ቻይናም ዛሬ ሰኞ ጉዞውን በተመለከተ ማረጋገጫ ሰጥታለች።

ስብሰባው ለፕሬዝደንት ሺ በፖለቲካ ረገድ ያላቸውን ተጽእኖ የሚያሳዩበት ሲሆን፣ ፑቲን ደግሞ ሩሲያ ወደ እሲያ እያዘመመች መሆኑን ለማሳየት ይጠቀሙበታል ተብሏል። የምዕራቡ ዓለም በዩክሬን ጦርነት ምክንያት ሩሲያን ለመቅጣት በሚፈልግበት በዚህ ሰዓት፣ ሁለቱ መሪዎች አጋጣሚውን በአሜሪካ ላይ ያላቸውን ተቃውሞ የሚያሳዩበት ይሆናልም ተብሏል።

XS
SM
MD
LG