በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ፕሬዚደንት ባይደን የ9/11 ሰምዓታትን ለመዘከር ተሰናድተዋል


ኒው ዮርክ በሚገኘው የ9/11 መታሰቢያ ስፍራ የተገኙ አሜሪካዊያንን ያሳያል ።
ኒው ዮርክ በሚገኘው የ9/11 መታሰቢያ ስፍራ የተገኙ አሜሪካዊያንን ያሳያል ።

ዩናይትድ ስቴትስ የዛሬ 21 ዓመት በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎቿን ያጣችበትን የአውሮፓዊያኑ መስከረም 11 ጥቃት በዛሬው ዕለት ትዘክራለች። ፕሬዚደንት ባይደን ቀኑን በማስመልከት ለህዝባቸው ንግግር እንደሚያደርጉ ፣ የአበባ ጉንጉንም ከጥቃቱ ስፍራዎች መካከል አንዱ በሆነው የአሜሪካ መከላከያ ሰራዊት መናገሻ ፔንታገን እንደሚያኖሩ ተነግሯል ።

በ2001 የጎረጎሳዊያኑ ዘመን ሽብርተኞች የንግድ አውሮፕላኖችን ጠልፈው እንደ ሚሳኤል በመጠቀም በኒዮርክ የዓለም ንግድ ማዕከል ህንጻ ላይ ፣ በዋሺንግተን ዲሲ ፔንታገን ህንጻ ላይ ጉዳት ጥቃት አድርሰዋል። በበረራ 93 ውስጥ የሚገኙ ተሳታፈሪዎች የያዘው አውሮፕላን ፔንሳልቪኒያ ግዛት ውስጥ በሚገኝ መስክ ላይ ተከስክሷል ።አልቃይዳ በፈጸመው በዚህ ጥቃት ወደ 3ሺ የሚጠጉ ሰዎች አልቀዋል። ዩናይትድ ስቴትስ እና አጋሮቿ በአጸፋው በአፍጋኒስታን ላይ ጦርነት አውጀዋል ።

ከፕሬዚደንት ባይደን በተጨማሪ ቀዳማዊ እመቤት ጂል ባይደን በሳንክስ ቪል ፔንሰልቫኒያ ፣ ምክትል ፕሬዚደንት ካምላ ሃሪስ እና ባለቤታቸው ወደ ኒዮርክ በማቅናት የጥቃቱን ሰለባዎች በሚያስታውሱ ስነስርዓቶች ላይ ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል ።

ዘገባው የአሶሼትድ ፕረስ ነው።

XS
SM
MD
LG