በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በኒውዮርክ ከተማ አቅራቢያ ተጨማሪ ቆሻሻ ውሃ ውስጥ የፖሊዮ ቫይረስ መገኘቱ ተገለፀ


በኒውዮርክ ከተማ፣ ኩዊንስ ኮሌጅ ውስጥ በሚገኝ ቤተ-ሙከራ አንድ ባዮሎጂስት የቆሻሻ ውሃ የተሰበሰበትን እቃ ይዞ ይታያል። በሐምሌ ወር በኒው ዮርክ ግዛት ሮክላንድ ካውንቲ በሽታው ከታየ ወዲህ በኒው ዮርክ ከተማ የቆሻሻ ፍሳሾች ውስጥ መገኘቱ ቫይረሱ እየተስፋፋ መሆኑን ያመለክታል።
በኒውዮርክ ከተማ፣ ኩዊንስ ኮሌጅ ውስጥ በሚገኝ ቤተ-ሙከራ አንድ ባዮሎጂስት የቆሻሻ ውሃ የተሰበሰበትን እቃ ይዞ ይታያል። በሐምሌ ወር በኒው ዮርክ ግዛት ሮክላንድ ካውንቲ በሽታው ከታየ ወዲህ በኒው ዮርክ ከተማ የቆሻሻ ፍሳሾች ውስጥ መገኘቱ ቫይረሱ እየተስፋፋ መሆኑን ያመለክታል።

ለህይወት አስጊ የሆነውን በሽታ የሚያስከትለው ቫይረስ በተለያዩ ከተሞች መገኘቱን ተከትሎ ፖሊዮን ለማዋጋት የሚደረገው ጥረት ተጠናክሮ መቀጠሉን በዩናይትድ ስቴትስ የኒውዮርክ ግዛት አስተዳዳሪ ካቲ ሆውኩል አርብ እለት አስታውቀዋል።


ከአስር አመት በኃላ ሐምሌ ወር ላይ በሰሜናዊው የኒውዮርክ ክፍል በሚገኘው ሮክላንድ ካውንቲ የመጀመሪያው የፖሊዮ ቫይረስ መገኘቱን ተከትሎ የጤና ባለሙያዎች በፍሳሽ ውሃዎች አካባቢ ቫይረሱ ይገኝ እንደሆን ምርመራ ማድረግ የጀመሩ ሲሆን በኒውዮርክ ምስራቃዊ ክፍል በሚገኘው ሎንግ አይላንድ ውስጥ፣ ናሳ የተባለ አካባቢ በተሰበሰበ ቆሻሻ ውሃ ውስጥ ቫይረሱ ተገኝቷል ። ቀደም ሲልም ሮክላንድ፣ ኦሬንጅ እና ሱሊቫን በተሰኙ ከተሰኙ አካባቢዎች ከተሰበሰበው ቆሻሻ ውሃ ውስጥ መገኘቱ ይታወሳል።

ይህን ተከትሎ ሆውኩል የጤና ሰራተኞች፣ አዋላጆች እና የመድሃኒት ባለሙያዎች የፖሊዮ ክትባት መስጠት ይሚያስችላቸው አስቸኳይ ግዜ አዋጅ አውጀዋል።

የጤና ባለሙያዎች ሁለት ወር የሞላቸውን ህፃናት ጨምሮ ያልተከተቡ የኒውዮርክ ነዋሪዎች፣ ነፍሰጡር እናቶች እና ሌሎች የክትባት ሂደታቸውን ያላጠናቀቁ በሙሉ በአስቸኳይ መከተብ እንዳለባቸው ያስታወቁ ሲሆን የጤና ሰራተኞች እና በፖሊዮ ከተጠቁ ሰዎች ጋር በቅርበት የሚሰሩ ሰዎች ደግሞ ተጨማሪ የማጠናከሪያ ክትባት እንዲወስዱ አሳስበዋል።

በኒውዮርክ ግዛት የሚኖሩ 79 ከመቶ የሚሆኑ ሰዎች የፖሊዮ ክትባት የወሰዱ ሲሆን ቫይረሱ በተገኘባቸው አካባቢዎች ክትባቱን የወሰዱ ሰዎች ቁጥር ግን ዝቅተኛ ነው። ባለስልጣናት በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በፖሊዮ ተይዘው ምንም ምልክት የማይታይባቸው ሊሆን እንደሚችል ገልፀው ሆኖም በቀናት እና በሳምንታት ግዜ ውስጥ ቫይረሱን ለሌሎ ሰዎች ሊያስተላልፉ እንደሚችሉ አመልክተዋል።

XS
SM
MD
LG