በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ድንበር የለሽ የሐረር ልጆች 3ኛ ዓመት ዝግጅት በቨርጂኒያ


ድንበር የለሽ የሐረር ልጆች 3ኛ ዓመት ዝግጅት በቨርጂኒያ
please wait

No media source currently available

0:00 0:10:58 0:00

ባላፈው ቅዳሜ አሌግዛንድሪያ ቨርጂኒያ ውስጥ ሦስተኛ ዓመታቸውን ያከበሩት “ድንበር የለሽ የሐረር ልጆች” በኢትዮጵያ፣ ሐረር ውስጥ ለሚገኙ የአንደኛ፣ መለስተኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህር ቤቶች የሚሰጡትን ድጋፍ አጠናክረው መቀጠላቸውን ገልጸዋል፡፡

የአሜሪካ ድምፅ ያነጋገራቸው የማህበሩ ቦርድ አባላት የመጠጥ ውሃ ጉድጎድችን እያስቆፈሩ፣ ኮምፒውተርን ጨምሮ ሌሎች የትምህርት መርጃ መሳሪያዎችን እየላኩ መሆኑንም ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል፡፡

በዝግጅቱ የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራሞች የተካሄዱ ሲሆን ተጋባዥ ምሁራንም የማኅበሩ አገልግሎት ስለሚጠናከርበት፣ ኢትዮጵያውያን ተማሪዎችና ትምህር ቤቶች የበለጠ መርዳት ስለሚቻልበት፣ ከያሉበት ሆነው ሙያዊ አስተያየቶቻቸውን ሰጥተዋል፡፡

ከተለያዩ የዩናይትድ ስቴትስ ክፍለ ግዛቶች የመጡት የሐረር ልጆች የዝግጅቱ ታዳሚ ነበሩ፡፡

XS
SM
MD
LG