በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ያገረሸው ጦርነት አሳሳቢነት


ያገረሸው ጦርነት አሳሳቢነት
please wait

No media source currently available

0:00 0:25:04 0:00

ሰላምም፣ ጦርነትም ያልነበሩባቸው አምስት ወራት አልፈው በፌዴራል መንግሥትና በትግራይ አማፅያን መካከል ጦርነቱ እንደገና አገርሽቷል።

ሞትና መፈናቀሉም እንዲሁ።

ሰሞኑን የወጡ ሪፖርቶች እንዳመለከቱት በመቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ተፈናቅለዋል። ይህ ከዚህ በፊት ተፈናቅለው ቋሚ መጠለያ በማጣት በጊዜያዊ መጠለያ እንደነገሩ የተጠለሉትንም ይጨምራል።

ለድጋሚ መፈናቀል ተዳርገዋል።

ነሃሴ 18 ላገረሸው ግጭት አንዱ ሌላውን ተጠያቂ ያደርጋል።

በሁለቱም ወገን ጥልቅ የሆነ ስሜታዊነት ይታይበታል የተባለው ይህ ጦርነት እንዲቆምና ለውይይት እንዲቀመጡ ሲደረግ የቆየው ጉትጎታ፤ እንዲሁም በዓለምአቀፍ ሸምጋዮች ከመቀሌ አዲስ አበባ ሲደረግ የነበረው ዲፕሎማሲያዊ መመላለስ ውጤት አልባ የሆነ ይመስላል።

ለዚህም አንዱ ወገን በሌላው ያመካኛል።

በቪኦኤም ሆነ በሌሎች መገናኛ ብዙኃን የተሰበሰቡ የህዝብ አስተያየቶች፣ ከዚህ ቀደም እንደነበረው በብዛት አንዱን ወገን ደግፈው የሚናገሩ ሳይሆኑ በአብዛኛው “ጦርነቱ ይብቃ፤ መከራው ይቁም” የሚሉ ናቸው።

ከሣምንት በላይ የቆየው ይህ ጦርነት የአየር ድብደባዎችን፣ “በሠራዊቴ ላይ በድንበሬ ውስጥ ጥቃት ተከፍቶብኛል” የሚሉ ክሶችን፣ ተጨማሪ መፈናቀሎችን፣ በማኅበራዊ ሚዲያ የሚደረጉ ወገን የለዩ የቃላት ጦርነቶችን አሰተናግዷል።

የጦርነቱ አንደገና መጀመር ብዙዎችን ቢያስጨንቅም፣ ግን ደግሞ ብዙዎችን አላስገረመም።

መጀመሪያውኑ ቆሞ ነበር ወይ? የሚሉም አሉ። ከነዚህ መሃል ፕሮፌሰር መሳይ ከበደ ይገኛሉ::

ፕሮፌሰር መሳይ ከበደ በኦሃዮ ዴይተን ዩኒቨርሲቲ የፍልስፍና መምህር ሲሆኑ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ጉዳዮች ብዙ ይፅፋሉ፤ ሃሳባቸውን ያንሸራሽራሉ።

XS
SM
MD
LG