የሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት እንደገና መቀስቀሱ በብሔራዊ የምክክር ሂደቱ ላይ ትልቅ ተግዳሮት መፍጠሩን የኢትዮጵያ አገራዊ ምክክር ኮሚሽን አስታውቋል።
ከኮሚሽኑ ኮሚሽነሮች አንዱ የሆኑት ዶ/ር ዮናስ አዳየ ለአሜሪካ ድምፅ እንዳሉት በዚሁ ጦርነት ምክንያት ለምሳሌ ትግራይን ወደ መሳሰሉ የአገሪቱ አካባቢዎች ሊያደረጉት ያሰቡት ጉዞ ተስተጏጉሏል።
ይህም ሆኖ ኮሚሽኑ ስራውንና ሂደቱን እንደሚቀጥል ኮሚሽነሩ አስረድተዋል።
የኢትዮጵያ አገራዊ የምክክር ኮሚሽን በዛሬው እለትም ከበባህር ዳር ከተማ ከተውጣጡ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ተወካዮች ጋር የአማራ ክልል ህዝብ ጥያቄዎች በሚል በተሰበሰቡ ነጥቦች ዙሪያ ውይይት አድርጓል።