በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሁለት ሳምንት የተቃረበው የሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት


ሁለት ሳምንት የተቃረበው የሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት
please wait

No media source currently available

0:00 0:08:45 0:00

እንደገና ከተቀሰቀሰ ዛሬ 13ኛ ቀኑን የያዘው የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት አሁንም እንደቀጠለ ነው። አስተያየታቸውን የሰጡን የሰቆጣ፣ የሁመራ እና የሌሎች አካባቢዎች ነዋሪዎች፣ ከአካባቢያቸው ራቅ ካሉ ሥፍራዎች የከባድ መሳሪያ ድምፅ እንደሚሰማ ተናግረዋል፡፡ ለጥቃቱ መስፋፋት በሁለቱ አካላት መካከል ያለው መወነጃጀል በቀጠለበት በአሁኑ ወቅትም የሰላም ጥሪዎችም እየቀረቡ ነው፡፡

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን የአፍሪካ ቀንድ ልዩ ልዑክ አምባሳደር ማይክ ሃመር በሰሜን ኢትዮጵያ ባለው ቀውስ ላይ ለመወያየት ወደ ኢትዮጵያ እየሄዱ መሆናቸውን ዋይት ሃውስ አስታውቋል።

በተያያዘ የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ባወጣው መግለጫ እንደገና የተቀሰቀሰው ጦርነት ቆሞ የሰላም ድርድር እንዲቀጥል” ጠይቋል።

XS
SM
MD
LG