በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በኒኮፖል ድብደባው ቀጥሏል

FILE - A man walks on a pedestrian crossing point near the Dnipro river and Zaporizhzhya nuclear plant on the other side in Nikopol, Ukraine, Aug, 22, 2022.
FILE - A man walks on a pedestrian crossing point near the Dnipro river and Zaporizhzhya nuclear plant on the other side in Nikopol, Ukraine, Aug, 22, 2022.

ኒኮፖል በተሰኘችው የዩክሬን ከተማ ያሉ በርካታ ነዋሪዎች፣ በአካባቢው በሚደረገው ከባድ የፈንጂ ድብደባ ምክንያት ምሽቶችን በድንኳንና መኪናቸው ውስጥ በማሳለፍ ላይ ናቸው።

ኒኮፖል በዣፖሪዢዥያ ከሚገኘው የኑክሌር ማመንጫ ጣቢያ በ 10 ኪ.ሜ ላይ የምትገኝ ከተማ ስትሆን፣ ላለፉት ሁለት ወራት ስትደበደብ ከርማለች።

ከዚህ በፊት ድብደባው በምሸት ሲካሄድ የነበረ ሲሆን፣ አሁን ግን በቀን ጭምር እየተካሄደ መሆኑን ነዋሪዎች ተናግረዋል ሲል አሶስዬትድ ፕረስ ዘግቧል።

በሩሲያ ሃይሎች ቁጥጥር ስር ያለው የዣፖሪዢዥያ ኑክሌር ማመንጫ ጣቢያ ከውጪ ከሚያገኘው የኤሌክትሪክ ሃይል መስመር ጋር ያለው ግንኙነት መቋረጡንና፤ እየቀጠለ ባለው ድብደባ ውስጥም ሆኖ፣ ጣቢያው ከውስጥ ባለው ተጠባባቂ የኤሌክትሪክ ሃይል እየተንቀሳቀሰ መሆኑን በተ.መ.ድ. የዓለም አቀፉ ኑክሌር ሃይል ባለስልጣን ሃላፊ የሆኑት ራፋኤል ግሮሲ ተናግረዋል።

ከኒኮፖል ነዋሪዎች ውስጥ ከ 50 በመቶ በላይ የሚሆኑት ከተማዋን ለቀው ሲወጡ፤ አንዳንድ ፋብሪካዎች አሁንም ስራ ላይ በመሆናቸው ወንዶች በከተማዋ ሲገኙ፣ ቤተሰቦቻቸው ግን ወደ አካባቢው በሚገኙ መንደሮች ለመሸሽ ተገደዋል።

XS
SM
MD
LG