በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የመጨረሻው የሶቪየት ኅብረት መሪ የሚኻዔል ጋርባቾቭ የቀብር ስነስርዓት ተፈጸመ


የመጨረሻው የሶቪየት ኅብረት መሪ የሚኻዔል ጋርቫቾቭ የቀብር ስነስርዓት
የመጨረሻው የሶቪየት ኅብረት መሪ የሚኻዔል ጋርቫቾቭ የቀብር ስነስርዓት

በሺዎች የሚቆጠሩ ሩሲያዊያን በዛሬው ዕለት የመጨረሻው የሶቪየት ኅብረት መሪ ለነበሩት ሚኻዔል ጋርቫቾቭ በክፍት የእሬሳ ሳጥን ውስጥ እንደተቀመጡ ስንብት አድርገዋል። ብዙዎቹም ‘ሰላም ያመጡ’ ሲሉ በማሞካሸት ጥቅልነትነት አስወግደው ነጻነታችንን ያቀዳጁን ናቸው ብለዋል።

ጋርባቾቭ እ.ኤ.አ 1985 -1991 ድረስ ሶቪየት ኅብረትን የመሩ ሲሆን ማክሰኞ ዕለት በ91 አመታቸው አርፈዋል። አስከሬናቸው በማዕከላዊ ሞስኮ ከእሳቸው የቀደሙት የሶቪየት ኅብረት መሪዎች ቭላድሚር ሌኒን እና ጆሴፍ ስታሊን ባረፉበት አርፏል።

በምዕራቡ ዓለም ‘ጎርቢ’ በመባል የሚቆላመጡት ጋርባቾቭ እ.ኤ.አ በ1990 ዓ.ም ቀዝቃዛውን ጦርነት በማስቆም ላበረከቱት አስተዋጽኦ የኖቤል የሰላም ሽልማት ተበርክቶላቸዋል። የቀብር ስነ-ስርዓታቸውም ኖቫያ የተሰኘው ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ እና የኖቤል ሽልማት የሰላም ሎሬት በሆኑት ዲሚትሪ ሙራቶቭ ተመርቷል።

የጋርባቾቭ ልጅ ኢሪና ከሁለት ልጆቻቸው ጋር በስነ-ስርዓቱ ላይ የተገኙ ሲሆን በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ታድመዋል። ይሁንና በቀብር ስነስርዓቱ ላይ ፕሬዘዳንት ቭላድሚር ፑቲን አልተገኙም።

ፕሬዝዳንቱ ሃሙስ ዕለት ለጋርባቾቭ አክብሮታቸውን ቢሰጡም ስራ የበዛበት መርሐ ግብራቸውን በመጥቀስ ከቅዳሜው የመታሰቢያ ዝግጅት እሳቸውም ሆኑ አጠቃላይ ክሬምሊን እርቀዋል።

ጋርቫቾቭ እንደ ጎርጎረሳዉያኑ አቆጣጠር በ2007 ከሞቱት እና ተቀናቃናቸው እንደሆኑት እንደ ቦርስ የልሲን የመንግስታዊ የቀብር ስነስርዓት አልተደረገላቸውም።

ይህንን ሁኔታ አስመልክቶ አንጋፋው ጋዜጠኛ ቭላድሚር ፖዝነር ለሮይተርስ እንደተናገረው "ይህ እራሱን የቻለ መግለጫ ይመስለኛል” ያለ ሲሆን "ፑቲን የጋርባቾቭ አድናቂ ናቸው ብዬ አላምንም። ሁለቱ ዓለምን የሚያዩበት መንገድ የተለየ ይመስለኛል።" ብሏል።

XS
SM
MD
LG