በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ማሊ የመንግስታቱ ድርጅት የሰብዓዊ መብት ሪፖርትን አጣጣለች  


በጎርጎሮሳዊያኑ ሚያዚያ 2022 የሩሲያ ወታደሮች አስክሬኖችን እየቀበሩ፤ በፈረንሳይ ወታደሮች በድሮን የተነሳ
በጎርጎሮሳዊያኑ ሚያዚያ 2022 የሩሲያ ወታደሮች አስክሬኖችን እየቀበሩ፤ በፈረንሳይ ወታደሮች በድሮን የተነሳ

የማሊ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የማሊ መንግስት በሰብዓዊ መብት ላይ ይፈጽማቸዋል ሲል ያወጣቸውን ክሶች እያጣጣለ ነው።

አስራ-አንድ ገጽ ባለው የማሊ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ባወጣው መግለጫ የመንግስታቱ ድርጅት የማሊ የጸጥታ ሃይሎች አድርሰውታል ባላቸው ክሶች ላይ ምላሽ ሰጥቷል።

ተ.መ.ድ ተልዕኮ በማሊ ሚንሱማ እሮብ ዕለት በዚህ ዓመት በሚያዝያ 1 እና ሰኔ 30 ባለው ጊዜ ውስጥ ተፈጸሙ ያላቸውን የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች ዙሪያ የሩብ ዓመት ማስታወሻ አውጥቷል። ሪፖርቱ በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ በማሊ ውስጥ የተፈጸሙት አብዛኛዎቹ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች የተፈጸሙት በእስላማዊ ታጣቂ ቡድኖች ቢሆንም በመንግስት የጸጥታ ሃይሎች "ከባድ የሰብዓዊ መብቶች እና የአለም አቀፍ የሰብአዊ ሕግ ጥሰቶች" መፈጸማቸውንም ተመዝግቧል ብሏል።

እ.ኤ.አ. ከ2022 የመጀመሪያ ሩብ አመት ጋር ሲነፃፀር የተመዘገቡ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች ቀንሰዋል። የማሊ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መግለጫ በመንግስት የጸጥታ ሃይሎች ላይ የተሰነዘረው ውንጀላ አድሏዊ ነው ያለ ሲሆን፤ ሪፖርቱ “ያለተጨባጭ ማስረጃ” እና “በአሸባሪዎች ስጋት ውስጥ የተፈጸመ” እንዲሁም ደግሞ “የመንግሥት የጸጥታ ኃይሎችን ስም ለማበላሸት” ዓላማ ያለው ነው ብሏል።

በማሊ ወታደራዊ መንግስት እና ሚኒሱማ መሃከል ያለው ውጥረት ከቅርብ ወራት ወዲህ እየጨመረ ነው። በሃምሌ ወር ማሊ ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት ድጋፍ ሊሰጡ የመጡ 49 የአይቮሪ ኮስት ወታደሮችን ባማኮ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ ቅጥረኛ ነፍሰ ገዳዮች ናቸው ስትል አስራለች።

በዛው ወር ላይ የመንግስታቱ ልዑክ በማሊ ቃል አቀባይ የመንግስታቱ ድርጅት የወታደሮችን መምጣት አስቀድሞ ለማሊ መንግስት አስታውቆ ነበረ የሚል ጽሁፍ በትዊተር ገጻቸው ላይ ካሰፈሩ በኋላ ከማሊ ተባረዋል።

XS
SM
MD
LG