በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

እርዳታ “ለታጣቂዎች እየዋለ ነው” ሲል የኢትዮጵያ መንግሥት ከሰሰ


እርዳታ “ለታጣቂዎች እየዋለ ነው” ሲል የኢትዮጵያ መንግሥት ከሰሰ
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:57 0:00

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት በአሁኑ ጦርነት “የህወሓት ምሽግ ውስጥ የተገኘ” ያለውን የአሜሪካ ባንዲራና የዩናይትድ ስቴትስ የዓለምአቀፍ ልማት ኤጀንሲ “ዩኤስኤአይዲ” ዓርማ ያለበትን የዕርዳታ ዱቄት ከረጢት የሚያሳይ ፎቶግራፍ በፌስቡክ ገፁ ላይ አጋርቷል።

ይህን በማስመልከት የአሜሪካ ኤምባሲ በኢሜይል በሰጠን ምላሽ የዩኤስኤአይዲ ዋና አስተዳዳሪ ሳማንታ ፓወር ከትናንት በስተያ በትዊተር ገፃቸው ወዳስተላለፉት “ማንኛውንም ዘረፋና ተቀባይነት የሌለው ጣልቃገብነት እንደሚያወግዙ” ወደገለፁበት መልዕክት መርቶን ተጨማሪ አስተያየት እንደማይሰጥ አሳውቋል።

ህወሓት ለዚህ ክስ ቀጥተኛ ምላሽ ባይሰጥም ከዚህ ቀደም የቀረቡበትን መሰል ውንጀላዎች ማስተባበሉ ይታወሳል።

በሌላ በኩል ይኸው በኢትዮጵያ ሰብዓዊ ቀውሱን እያባባሰ ነው የተባለው “ጦርነት እንዲቆምና ድርድር እንዲጀመር፣ የትግራይ ተዋጊዎች በአማራ ክልል የሚያደርጉትን ውጊያ ባስቸኳይ አቁመው ወደ ትግራይ እንዲመለሱ፣ የኤርትራ ኃይሎችም ከትግራይ እንዲወጡ፣ የኢትዮጵያ መንግሥትም በትግራይ መሠረታዊ አገልግሎቶችን እንዲያስጀምር” ስትል ዩናይትድ ኪንግደም ጠይቃለች።

የኢትዮጵያ የኃይማኖት ተቋማት ጉባዔም የጦርነቱ ተፋላሚ ወገኖች ተኩስ እንዲያቆሙና ያለምንም ቅድመ ሁኔታ የሰላም ንግግሮችን እንዲቀጥሉ ጠይቋል።

XS
SM
MD
LG