በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአሁኑ ጦርነት ያስከተለው የህፃናት ሞትና መፈናቀል


የአሁኑ ጦርነት ያስከተለው የህፃናት ሞትና መፈናቀል
please wait

No media source currently available

0:00 0:09:34 0:00

በሰሜን ኢትዮጵያ ያገረሸውን ጦርነት ተከትሎ ከ200 ሺህ በላይ ሰዎች መፈናቀላቸውን የአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት አስታውቋል።

ህወሓት በያሎ ከተማ ላይ ተኩሷል ባሉት ከባድ መሣሪያ ሦስት ሕፃናት መገደላቸውንና የቆሰሉት በዱብቲ ሆስፒታል እየታከሙ መሆናቸውን የክልሉ የአደጋ ሥጋት ሥራ አመራርና የምግብ ዋስትና ኮሚሽነር መሀመድ ሁሴን ለአሜሪካ ድምፅ አክለው ገልፀዋል።

በአካባቢው በተፈፀመው ድብደባ ሕፃናትን መገደላቸውን የተባበሩት መንግሥታት የሕፃናት መርጃ ድርጅት /ዩኒሴፍ/ አመልክቶ በአስቸኳይ ተኩስ እንዲቆም ጥሪ አሰምቷል።

ህወሓት ሲቪሎችን ዒላማ በማድረግ የሚቀርቡበትን ውንጀላዎች በተደጋጋሚ ያስተባብላል።

በሌላም በኩል ካለፈው ሣምንት ጀምሮ በአስቸጋሪ ሰብዓዊ ሁኔታ ውስጥ መሆናቸውን ሰሞኑን ከቆቦ ከተማ የተፈናቀሉ ተናግረዋል።

XS
SM
MD
LG