የሁለቱ የሊቢያ ተቀናቃኝ መንግሥቶች ታማኝ ሚሊሽያዎች ዋና ከተማይቱ ትሪፖሊ መሀል ላይ ባካሄዱት ውጊያ ብዙ ሰው መገደሉን የሃገሪቱ መገናኛ ብዙኃን ዘገቡ።
ምሥራቃዊውን የአገሪቱን ክፍል የያዙት የጠቅላይ ሚኒስትር ፋቲ ባሻጋ ደጋፊዎች የዋና ከተማይቱን አንዳንድ ክፍሎች ሲቆጣጠሩ ከተሰናባቹ ጠቅላይ ሚኒስትር አብዱልሃሚድ ድቢባህ ወገን የሆኑ ኃይሎች በበኩላቸው አሁንም ስፋት ያለውን አካባቢ እንደያዙ መሆናቸው ተገልጿል።