በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አልሸባብ በኬንያ ላይ ጥቃት ለመፈጸም ዛተ


ምስሉ በጎረጎሳዊያኑ ጥቅምት 25 /2016 ማንዴራ በተባለው የሀገሪቱ ስፍራ የቦንብ ጥቃት ከደረሰ በኃላ ፣ የኬንያ የመከላከያ ሰራዊት አባላትን ስምሪትን ያሳያል። ለጥቃቱ አልሸባብ ኃላፊነት ወስዷል ።
ምስሉ በጎረጎሳዊያኑ ጥቅምት 25 /2016 ማንዴራ በተባለው የሀገሪቱ ስፍራ የቦንብ ጥቃት ከደረሰ በኃላ ፣ የኬንያ የመከላከያ ሰራዊት አባላትን ስምሪትን ያሳያል። ለጥቃቱ አልሸባብ ኃላፊነት ወስዷል ።

መቀመጫውን ሶማሊያ ውስጥ ያደረገው፣ ከአልቃይዳ ጋር ትስስር ያለው እስላማዊ የታጣቂዎች ቡድን አልሸባብ በኬንያ ላይ አዲስ የዛቻ መግለጫ አውጥቷል። ቡድኑ ፣ ኬንያ ወታደሮቿን ከሶማሊያ እስካላስወጣች ድረስ በሀገሪቱ ላይ ጥቃቱን እንደሚቀጥል አስታውቋል ።አልሸባብ በእንግሊዝኛ ቋንቋ ባወጣው መግለጫ የኬንያ ከተሞች ላይ ያነጣጠረ ጥቃት እንደሚፈጽም አስጠንቅቋል።

የኬንያ መንግስት የሙስሊሞችን ምድር ወረራን ካስቀጠለ ፣ በሀገሪቱ ውስጥ “ጥቃት መፈጸሙን እቀጥላለሁ ”ብሏል።“መሬታችንን እና ህዝባችንን ከጉልበተኛው የኬንያ ወረራ መከላከላችንን እንደምንቀጥል ሊታወቅ ይገባል” ሲል አክሏል አልሸባብ ።

ኦማር ሞሃመድ የተባሉት የዓለም አቀፉ ቀውስ ቡድን የምስራቅ አፍሪካ ከፍተኛ ተንታኝ፣ አልሸባብ የኬንያን ድንበር በማጣስም ሆነ በሌሎች የሀገሪቱ ከተሞች ላይ የሽብር ጥቃቶችን በማድረስ ለኬንያ ስጋት ሆኖ መቆየቱን በማስታወስ ፣ ቡድኑ የፈለገውን እስካለገኘ ድረስ ጥቀዋት ማድረስ መቀጠሉ አይቀሬ እንደሆነ ለአሜሪካ ድምጽ በዋትሳፕ መገናኛ በኩል አስረድተዋል።

መቀመጫውን ሞጋዲሹ ላይ ያደረገው የራድ ሰላም ጥናት ተቋም ኃላፊ የሆኑት ሞሃመድ ሁሴን ጋስ በበኩላቸው ፣የአፍሪካ ህብረት ኃይሎች ሶማሊያ ውስጥ ቢኖሩም ቡድኑ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ የበለጠ መጠንከሩን ፣ ኢትዮጵያ ውስጥ በቀጠለው የእርስበርስ ጦርነት ምክንያት በቀጠናው አለመረጋጋት መባባሱን ፣ፖለቲካዊ እና ማህበራዊ ጽንጽ አለመረጋጋቱን የበለጠ ሊያባብሰው እንደሚችል ጠቁመው ፣ ቡድኑ በቅርቡ በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ላይ የከፈተው ጥቃት ከሶማሊያ ውስጥ እና ከሶማሊያ ውጪ ለመስፋፋት ያለው ፍላጎት ማየሉን አመላካች መሆንን ለአሜሪካ ድምጽ በስልክ አስረድተዋል።

አልሸባብ የሶማሊያ መንግስት እና የአፍሪካ ህብረት የሰላም ማስከበር ተልዕኮዎችን ከ15 ዓመታት በላይ ተፋልሟል።

XS
SM
MD
LG