በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ተመድ የኒዩክለር መርማሪዎችን ወደ ዛፖሮዥዢያ ሊልክ ነው


የዛፖሮዥዢያ የኒዩክለር ኃይል ማመንጫ ጣቢያ
የዛፖሮዥዢያ የኒዩክለር ኃይል ማመንጫ ጣቢያ

ዩክሬን ውስጥ ዓለም አቀፍ መርማሪዎች ለአደጋ የተጋለጠውን በዛፖሮዥዢያ የኒዩክለር ኃይል ማመንጫ ተቋም ለመመመልከት ዝግጅት በማድረግ ላይ በሚገኙበት በአሁኑ ወቅት በተቋሙና በአካባቢው ከፍተኛ ውጥረት መስፈኑ ተነገረ፡፡

ሩሲያና ዩክሬን ሁለቱም በአውሮፓ ትልቁ የኒዩክለር ተቋም ወደሆነው ስፍራ ከባድ የጦር መሳሪያዎችን ተኩሰዋል በሚል እርስ በርስ እየተወነጃጀሉ መሆኑም ተመልክቷል፡፡

የተባበሩት መንግሥታት ዓለም አቀፍ የአቶሚክ ኤነርጂ ተቋም የኒዩክለር ተቋሙን የሚመለከቱ መርማሪ ልኡኮችን በቅርቡ ወደ ስፍራው ይላክ ተብሎ እንደሚጠበቅ ተነገሯል፡፡

ባላሥልጣናት ከኒውከለር ተቋሙ የተወሰነው ክፍል ቢመታ አፈትልከው የሚወጡ የረዲዮ ጨረሮች ሊኖሩ ይችላል የሚል ሥጋት ያደረባቸው መሆኑም የቪኦኤው ክሪስ ሲምከን ዘገባ አመልክቷል፡፡

የዛፖሪዥዢያው የኒዩክለር ተቋም በሩሲያው ወታደሮች ቁጥጥር ከሆነበት ጊዜ ጀምሮ የጦር ቀጠና በሆነው በአካባቢው ከፍተኛ ውጥረት መስፈኑ ተመልክቷል፡፡

XS
SM
MD
LG