በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

መንግሥትና ህወሓት በሠላም ጥረቱ ላይ እየተወዛገቡ ነው


መንግሥትና ህወሓት በሠላም ጥረቱ ላይ እየተወዛገቡ ነው
please wait

No media source currently available

0:00 0:11:31 0:00

ከሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት በኋላ “የትግራይ ኃይሎች ወታደራዊ ኮማንድ” የሚል ስያሜ ያለው ትግራይ ክልልን በማስተዳደር ላይ የሚገኘው አካል ባወጣው መግለጫ፤ “ለሰብዓዊነት ሲባል ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር የተደረገውን የተናጥል የተኩስ ማቆም ሥምምነት የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ጥሶታል” ሲል አስታወቀ።

“ሰኞ ነሐሴ 9/2014 ዓ.ም የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት በትግራይ ሠራዊት ላይ ለአንድ ሰዓት የቆየ የከባድ ጦር መሳሪያ ድብደባ ፈፅሟል” ሲል ክልሉ በመግለጫው ክስ አሰምቷል።

በክልሉ የውጭ ግንኙነት እየተባለ የሚጠራው ጽ/ቤት ከፍተኛ አመራር ፕሮፌሰር ክንደያ ገ/ሕይወት መግለጫውን በተመለከተ ለአሜሪካ ድምፅ በሰጡት ማብራሪያ፤ የትግራይ ክልል ፍላጎች ችግሮች በሰላማዊ መንገድ እንዲፈቱ መሆኑን ገልፀው ነገር ግን ሁኔታዎች እልባት ማግኘት እንዳልቻሉ ተናግረዋል።

በሌላ በኩል በትግራይ ክልል የተቋረጡ መሠረታዊ አገልግሎቶችን እንደገና ማስጀመር የሚቻለው ሊያሠሩ የሚችሉ ሁኔታዎች ሲፈጠሩ መሆኑን የጠቅላይ ሚኒስትር ጸ/ቤት የፕሬስ ክፍል ኃላፊ ቢል ለኔ ስዪም ተናግረዋል።

ቢል ለኔ ይሄንን የተናገሩት ዛሬ ለውጭ የመገናኛ ብዙሃን ዘጋቢዎች በሠጡት መግለጫ ነው።

የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ትንኮሳና ጥቃት እየፈጸመብን ነው በሚል በህወሓት የቀረበውን ውንጀላም የፕሬስ ኃላፊዋ አጣጥለዋል።

የህወሓት ቃል አቀባይ ጌታቸው ረዳ “የኢትዮጵያ ፌዴራል መንግሥት መሠረታዊ አገልግሎቶችን ማስቀጠልን ጨምሮ ለሠላም ውይይት ምቹ ሁኔታ አልፈጠረም” በማለት ወንጅለዋል።

አቶ ጌታቸው በትዊተር ገጻቸው ላይ ባሠፈሩት ጹሑፍ “የፌዴራል መንግሥቱ ለሠላም ፍላጎት የለውም” በማለትም ተችተዋል።

የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት የፕሬስ ሃላፊ ቢልለኔ ስዩም ግን መሠረታዊ አገልግሎቶችን መቀጠልና ማቋረጥ ከማዕከል በማብሪያና ማጥፊያ ቁልፍ የሚቆጣጠሩት ዓይነት ጉዳይ እንዳልሆነ በማስታወስ የራሱ አካሄድ እንዳለው ተናግረዋል።

XS
SM
MD
LG